Tender Detail

Tender Details

  • Company ብርሃን ናትና የበጎ አድራጎት ድርጅት
  • Address አክሱም ከተማ የድርጅቱ ዋና ቢሮ ፡ ትግራይ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0914764145
  • Website
  • Deadline25 May 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price
  • opening date2026-05-26 10:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

ብርሃን ናትና የበጎ አድራጎት ድርጅት በሕጋዊ የውጭ ኦዲቶሮች የድርጅቱን የአንድ ዓመት ኦዲት ለማድረግ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር BNCO/001/08/2018

 

ብርሃን ናትና የበጎ አድራጎት ድርጅት በሕጋዊ የውጭ ኦዲቶሮች የድርጅቱን የአንድ ዓመት ኦዲት ለማድረግ ስለፈለገ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸዉ ተወዳዳሪዎች የቴኒካልና የፋይናንስ ሁለት የተለያዩ ፕሮፖዛል በማቅረብ በግልፅ ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው፡-

1.     በውጭ ኦዲት ሞያ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ ቲን ነምበር፣ ቫት ተመዝጋቢ መሆኑንና ሌሎች አስፈላጊ ዶክመንት የሚያቀርብ

2.     የጨረታ ሰነዱን ከብርሃን ናትና በጎ አድራጎት ድርጅት ቢሮ ከትግራይ ክልል አክሱም ከተማ መውሰድ የሚችል

3.     ሁለት የጨረታ ፕሮፖዛል ሊያቀርብ የሚችል ሁኖ አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ ቴክኒካል ፕሮፖዛል እንዲሁም አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንስ ፕሮፖዛል ሁለቱም በተለያየ ፖስታ በስርዓት ታሽጎ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት

4.     የጨረታው ግምገማ መጀመሪያ ኒካል ፕሮፖዛል የሚታይ ሁኖ ዝቅተኛውን መስፈርት ያሟላ ተወዳዳሪ የፋይናንስ ፕሮፖዛሉ ተከፍቶ ይታያል ሆኖም ግን ዝቅተኛ የቴክኒካል መስፈርት ያላሟላ ተወዳዳሪ የፋይናንስ ፕሮፖዛል አይከፈትም

5.     ቴክኒካል ፕሮፖዛል ተወዳዳሪዎች በአካል ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ይከፈታል

6.     የጨረታ ሰነዱ በአማርኛ ወይም በኢንግሊዘኛ መቅረብ ይችላል

7.     ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን 10 የሥራ ቀን በኋላ ባለው ቀጣይ የሥራ ቀን ሆኖ በጨረታ ሰነድ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል እንዲሁም የሚከፈተው በአክሱም ከተማ የድርጅቱ ዋና ቢሮ መሆኑን እናሳውቃለን

8.     ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መከፈት እያስተጓጉልም

9.     ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

ተጨማሪ መረጃ፡-

በስልክ ቁጥር 0914764145/0911709522 ደውለው ይጠይቁ

 

ብርሃን ናትና የበጎ አድራጎት ድርጅት

Save Tender