በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒከና ሳተላይት ኢንስቲትዩት በ2018ዓ/ም የሥልጠና ዘመን በተመደበለት የካፒታል በጀት እና SEED (ሲድ) ከተባለ ግብረ - ሠናይ ድርጅት በተመደበለት በጀት ለተለያዩ ዲፓርትመንቶች ለአጫጭር ጊዜ ሥልጠና አገልግሎት የሚውል ቋሚ የሥልጠና መሣሪያ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒከና ሳተላይት ኢንስቲትዩት በ2018 ዓ/ም የሥልጠና ዘመን በተመደበለት የካፒታል በጀት እና SEED (ሲድ) ከተባለ ግብረ - ሠናይ ድርጅት በተመደበለት በጀት ለተለያዩ ዲፓርትመንቶች ለአጫጭር ጊዜ ሥልጠና አገልግሎት የሚውል ቋሚ የሥልጠና መሣሪያ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛቹኋል፡፡
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላትና ፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ ማረጋገጫ የሚያቀርብ፣ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት/፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች የቲን ቁጥር /tin Number/ ያለው /ያላት
2. በመንግሥት ግዥ አቅርቦት የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስከር ወረቀት ያለው/ያላት
3. የዕቃውን ዋጋ በኮሌጁ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ ገፁን ሳይገነጣጥል ሞልቶ የሚያቀርብ
4. የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ የዕቃዎች መለያ /specification/ ኮሌጁ ባዘጋጀው መሠረት ብቻ የሚያቀርብ/የምታቀርብ ፣
5. የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፣
6. ተጫራቾች የጨረታ ማከበሪያ ዋስትና ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር ብቻ/ በባንከ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ /CPO/ ከእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ጋር በማሸግ ማቅረብና ማስያዝ ይገባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን /Bid Document/ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአ/ም/ጭ/ ፖ/ቴ/ሳ/ ኢንስቲትዩት ክ/ሂ/ደ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን፣ ማህተምና አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው።
9. አጠቃላይ የማስረጃቸውን ኮፒ ከዋናው ጋር ተገናዝቧል የሚል ማህተም አርፎበት እና ተፈርሞበት ተያይዞ መቅረብ አለበት፣
10. የሚቀርበው የመወዳደሪያ ሰነድ በሁለት ኮፒ ተዘጋጅቶ የዕቃው ነጠላ ዋጋ በአንድ ላይ በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ/ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን ከገዙበት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ቀን የሚያበቃው የሥራ ቀን ከሆነ በ15ኛ ቀን ከቀኑ በ10፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በቀጣዩ ቀን ልክ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የታሸገው ሣጥን በአ/ምንጭ ፖሊ ቴክኒከ ሳታላይት ኢንስቲትዩት በቢሮ ቁጥር 7 ይከፈታል ቀኑ በዓል (ዝግ) ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
11. ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ የዋጋ ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡ እንዲሁም ከስፔስፊኬሽን ውጪ ዕቃ ማቅረብ አይቻልም፡፡
12. አሸናፊዎች የዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝና ውል መፈራረም አለባቸው።
13. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ ማቅረብና ማስረከብ አለበት፡፡
14. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. የተጭበረበረ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም በሕግም ያስቀጣል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0468810960/0910744129/0912056962
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ሳተላይት ኢንስቲትዩት
