Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት
  • Address ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-06 ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ: አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0911924597
  • Website
  • Deadline05 Jun 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2026-06-05 10:30:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ሶማሌ ተራ አካባቢ በተቋሙ ስም ያለውን ክፍት ቦታ ለፓርኪንግ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

 

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ሶማሌ ተራ አካባቢ በተቋሙ ስም ያለውን ክፍት ቦታ ለፓርኪንግ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ሕጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብቻ ጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሰነዱን አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህጻናት እና ወጣቶች የቴአትር እና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ህንጻ 3 ፎቅ ግዢ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ትችላላችሁ፡፡

1.     የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል የዘመኑን ግብር የከፈለ፡፡

2.     በዘርፉ የተሰማሩበት ንግድ ፍቃድ፡፡

3.     የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4.     በዘርፉ በቂ ልምድ ያለው

5.     ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ማህተም እና ፊርማቸውን በሰነዱ ላይ ማኖር ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህም አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 230 - 1130 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡

6.     የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ብቻ ማሲያዘ አለባቸው

7.     ተጫራጮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቅዳሜ ጨምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8.     ጨረታው 11ኛው ቀን 400 ተዘግቶ 430 ይከፈታል፡፡

9.     ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህጻናት እና ወጣቶች ቴአትር እና ሲኒማ ኮምፕክስ 3 ፎቅ እና ንብረት አስተዳደር

መረጃ ስልክ ቁጥር 09-11-92-45-97/09-91-75-12-12

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት

Save Tender