Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Pipe Factory (APF) (የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ማህበር)
  • Address ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09-35-98-37-29
  • Websitehttps://www.amharapipe.et/
  • Deadline08 Jun 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-06-08 14:30:00
  • Categories Accounting & Auditing

አማራ ፓይፕ ፋብሪካ የግል ኩባንያ በበጀት ዓመቱ የERP Software የተገበረ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴውን በIFRS መሠረት በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው የሂሳብ ምርመራ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡


የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር - APF/22/2018/Local

 

አማራ ፓይፕ ፋብሪካ የግል ኩባንያ በበጀት ዓመቱ ERP Software የተገበረ ሲሆን 2018 በጀት ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴውን IFRS መሠረት በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው የሂሳብ ምርመራ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1.     2018 በጀት ዓመት በሙያው የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የተሰጠ የታደሰ የኦዲት ሙያ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት እና VAT ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2.     የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከፋብሪካው የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

3.     ተወዳዳሪ ድርጅቶች የተወዳደሩበትን የአገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ VAT ጨምሮ 2% ባህርዳር ከተማ ውስጥ ባለ የባንኩ ቅርንጫፍ በኩል ማረጋገጫ የተሰጠበት የጨረታ ማስከበሪያ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Irrevocable & unconditional Bank Guarantee) በፋብሪካው ስም "Amhara Pipe factory Plc” በማሰራት ማቅረብ አለባቸው፡፡

4.     ተጫራቾች የሕጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ኮፒ እና ሌሎች የቴኒክ መወዳደሪያ ሠነዶችን በአንድ ላይ (Technical Bid Offer) በማለት ለብቻው ከዋጋ ማቅረቢያው (Financial Bid Offer) በመለየት በፖስታ በማሸግ (ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5.     እንዲሁም ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን (Financial Bid Offer) እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን ለብቻው ከላይ በተ. 4.1 ላይ ከተገለፁት ከቴኒክ መስፈርት በመለየት በፖስታ በማሸግ (ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 15ኛው ቀን ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 800 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 830 የቴኒክ የመጫረቻ ሠነድ ብቻ ይከፈታል።

7.     15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይሆናል፡፡

8.     ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

9.     በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ፋብሪካው ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09-35-98-37-29/09-18-70-18-26 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ /የተ/የግ/ ኩባንያ

Save Tender