Tender Detail

Tender Details

  • Company Hidasie Telecom Share Company
  • Address , Phone: 00 00 00 00
  • Website
  • Deadline16 Jun 2026, 4:18 PM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-05-27 16:18:00
  • Categories Accounting & Auditing

ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የፋይናንስ አማካሪ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የፋይናንስ አማካሪ አገልግሎት ግዥ

ለ2ግዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር፡RE-LT/HT/HO/05/2026

  1. ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የፋይናንስ አማካሪ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 20 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 09 ቀን 2018ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10፡00 ድረስ ቅዳሜ ከጠዋቱ 230-600 “ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ” ጠመንጃ ያዥ ንግድ ባንክ አጠገብ ቴሌ ጋራዥ ግቢ ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮቁጥር 211 በመቅረብ የማይመለስ ብር00 /ሶስት መቶ/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት፡-
  • አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ፣
  • አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
  • ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በሰም የታሸገ መሆን አለበት፣
  • በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
  1. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ብቻ ለሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን ሰኔ 9 ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 211 ሲሆን፣ ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ሰኔ 09ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 211 ይሆናል::
  3. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ያልተከተሉ ተጫራቾች ወዲያውኑ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ እንደሚሆኑ እንገልጻለን፡፡
  4. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0968135675 ወይም 0968271291 መጠቀም ይችላሉ፡፡
  5. ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር

Save Tender