በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ የፋብሪካ መለዋወጫዎችን ማለትም ሎት 1 የተለያዩ ዓይነት ቤሪንግ፣ ሎት 2 የተለያዩ የመካኒካል አላቂ ዕቃዎች፣ ሎት 3 የተለያዩ ኤሌክትሮዶች፣ ሎት 4 የተለያዩ ዓይነት የመካኒካልና ኤሌክትሪካል መለዋወጫዎች፣ ሎት 5 ኤሌክትሪካል መለዋወጫዎች፣ ሎት 6 የተለያዩ የኤሌክትሪካል አላቂ ዕቃዎች፣ ሎት 7 የተለያዩ አይ
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡--አግጨ-006/ኦኩስፋ -2/2018
1. በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ የፋብሪካ መለዋወጫዎችን ማለትም ሎት 1 የተለያዩ ዓይነት ቤሪንግ፣ ሎት 2 የተለያዩ የመካኒካል አላቂ ዕቃዎች፣ ሎት 3 የተለያዩ ኤሌክትሮዶች፣ ሎት 4 የተለያዩ ዓይነት የመካኒካልና ኤሌክትሪካል መለዋወጫዎች፣ ሎት 5 ኤሌክትሪካል መለዋወጫዎች፣ ሎት 6 የተለያዩ የኤሌክትሪካል አላቂ ዕቃዎች፣ ሎት 7 የተለያዩ አይነት ስታር ቡሽንጎች ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ20 ቀን የባንክ ዋስትና /BID BOND/ በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር /supplier List/ ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ ስድስተኛ ቀን ይከፈታል፡፡ የጨረታውን መክፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ለሁሉም ጥቅል የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10:30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት፤ ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ በተመለከተው ነው።
5.1 ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ የስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነኦ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ፡፡
ስልክ ቁጥር: 09-91-14-94-85/09-/0930856415
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ሎት የማስከበሪያ ዋስትና ለሁሉም ሎቶች አንድ ላይ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. የዕቃ ርክክብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ አዲስ አበባ ማስተባበሪ ቢሮ ነው።
8. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው።
9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው፡፡
10. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ Tel-0940209464 ሀይል ውሃ
አዲስ አበባ ግዥ ማስተባበሪያ ቢሮ Tel: 09-91-14-94-85/0930856415
አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ
