የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈዉ የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 03/10/2018 እና 06/10/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈዉ የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 03/10/2018 እና 06/10/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላካሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
የጨረታ መስፈርቶች፡-
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅሰቃሴያቸዉን ለታክስ ማዕከሉ ያሳውቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸዉ የምሰክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል
|
ተ.ቁ |
የጨረታ ቦታ |
የጨረታው ዓይነት |
የጨረታው የቀረቡ ዕቃዎች |
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታና በሐራጅ |
ጫማዎች አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ፣ የስፖርት ዕቃዎች፣ የእጅ ሰዓት ኮስሞቲክስ፣ መነጽር፣ ጠፍጣፋ ብረቶችና ፕላስቲኮች እና ሌሎች ላሜራ፣ የወዳደቁ ልዩ ልዩ ዕቃዎች |
ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ 03/10/2018 እና 06/10/2018 እስከ ጠዋቱ 3፡45 ሰዓት |
ለግልጽ ጨረታ 03/10/2018 እና 06/10/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 03/10/2018 06/10/2018 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል። |
2. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 03/10/2018 እና 06/10/2018 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላከሎት ማድረግ ይችላሉ፡፡
3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንከ አሰርተዉ በአዋሽ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ሰም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እሰኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡
5. የጨረታፊ መክፈቻ ቦታ፡- በቃሊቲ ጉ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (cpo) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሰራ ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
7. ከአሸፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውሰጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
