Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline20 Jun 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2026-06-20 10:30:00
  • Categories Printing And Publishing , Printer And Photocopy Machine

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡ኢፕድ 025/2018/

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1. የዳይሪክትሪ መፅሀፍ ህትመት

ሎት 2. የመፅኄት ህትመት ስራ

ሎት 3. ወረቀት

ሎት 4. የፎቶ አክለሪክ ህትመት

ስለሆነም፡ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

1.     በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

2.     ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብርለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዢ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ 16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

3.     ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበርያ የሚውል ብር

1.     ለሎት 1 ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ)

2.     ለሎት 2.ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ)

3.     ለሎት 3 ብር 30,0000.00(ሰላሳ ሺህ)

4.     ለሎት 4 ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህበባንክ በተረጋገጠ ../ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው።

5.     ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ 400 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 430 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አንደኛ ፎቅ አቅርቦት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

6.     /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡- 011 156 9869

.ሜይል procurement@press.et

አድራሻ፡አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

Save Tender