የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በባሶና ወራና ወረዳ አባሞቴ ቀበሌ ልዩ ስሙ ወንበር አምባ ደን ቦታ ላይ ለፋብሪካ ግብዓት የማይውል የግንድ ተረፈ ምርት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በባሶና ወራና ወረዳ አባሞቴ ቀበሌ ልዩ ስሙ ወንበር አምባ ደን ቦታ ላይ ለፋብሪካ ግብዓት የማይውል የግንድ ተረፈ ምርት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝርመረጃ መሰረት መወዳደር የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡
1. የተረፈ ምርቱን አይነት እና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታው መመሪያ ሰነድ ማግኘት ይቻላል ወይም በደን ቦታ ላይ በአካል በመገኘት ማየት ይቻላል፤ የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ 200 ብር ከፍሎ መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታው መመሪያ ላይበተገለፀው የብር መጠን መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋጋውን እና አስፈላጊ መረጃዎችን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይየካላንደር ቀናት አየር ላይ ይሆናል፤ ሆኖም ግን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
5. የጨረታ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ወይም በማግስቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾቹ ከሥራ መስኩ ጋር ተያያዥነት ያለው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የVAT እና TIN ሰርተፊኬት የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፤ በውከልና የሚወዳደሩ አካላት ከፍትህ ወይም ከሰነዶች ማረጋገጫ ህጋዊ የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
v ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116375803 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ
ኃ/የተ/የግ/ማህበር
