ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ሽፍሻፊ ወረቀት፣ ቁርጥራጭ ወረቀት፣ አገልግሎት የሰጠ ንብረቶች ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ሽፍሻፊ ወረቀት፣ ቁርጥራጭ ወረቀት፣ አገልግሎት የሰጠ ፕሌት፣ የተፈጨ ወረቀት፣ ፊልም፣ ኮር፣ አገልግሎት የሰጠ ፊከሰር፣ አገልገሎት የሰጠ ፕሬስ ላይን በርሜል፣ የጥቅል ዕላቂ፣ ትልቅ የቀለም ቆርቆሮ፤ ትንሽ የቀለም ቆርቆሮ፣ የቀለም ባልዲ፣ አ/ት የሰጠ የብረት በርሜል፣ ግፋፊ ወረቀት፤ በኅትመት የተበላሸ ጋዜጣ፣ ሊድ፣ በኅትመት የተበላሸ መጽሐፍ፣ የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪ፣ የተለያዩ የፎርክ ሊፍት ጐማዎችና ከመነዳሪዎች፤ የተቆራረጡ ጎልድ ፎይል፣ የፎርከ ሊፍት በነፋስ የሚሠራ ጐማ፣ የፎርክ ሊፍት ጐማ ፍላፕ፣ ሊዶች፣ አገልግሎት የሰጡ ጐማዎች፣ አሸንዳ፣ አገልግሎት የሰጡ ተሽከርካሪዎች፣ አ/ት የሰጡ ቶነሮች፣ አ/ት የሰጡ ወንበሮች፣ አ/ት የሰጡ ፕሪንተርና ኮምፒውተር፣ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፤
2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን ድረስ በዋናው ቅጥር ግቢ በሚገኘው የማርኬቲንግ ሽያጭ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመምጣት የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 300 በመከፈል መግዛትና ንብረቶቹንም ማየት ይቻላል።
3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
4. ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዛበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መከተት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በ
ከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት
