Tender Detail

Tender Details


የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በ2018 በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የሽያጭና የአገልግሎት ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለመሸጥ ይፈልጋል ፡-


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር009/ሽያጭና አገልግሎት/18 .

 

የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት 2018 በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የሽያጭና የአገልግሎት ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለመሸጥ ይፈልጋል -

        1ኛ. ለምግብነት የሚውል ስንዴ፣ ቦቆሎ፣ ብጣሪዎች እና ያገለገሉ ፖል ባግ ሽያጭ ለመጀመርያ ጊዜ

        2ኛ. 2017 እና 2018 የድርጅቱን ሂሳብ በውጭ ኦዲተሮች ለማስመርመር ለሶስተኛ ጊዜ

        3ኛ. የሠራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ ለሶስተኛ ጊዜ

በዚሁ መሰረት፡

·        ተጫራቾች በሥራ ዘርፉና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች ህጋዊ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና የዘመኑን የመንግሥት ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

·        ተጫራቾች ለጨረታው ውድድር ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለጽ ይሆናል።

·        የጨረታው ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 400.00 በመክፈል በሀዋሳ ከተማ በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ።

·        ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ፖስታ/ኤንቨሎፕ/ በማድረግ ኦሪጂናልና ኮፒውን ለየብቻው ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በድርጅቱ የግዥ ፋይ//አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ 10ኛው ቀን እስከ 800 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።

·        የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 10ኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ታሽጐ በእለቱ 830 ሰዓት በድርጅቱ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል።

·        ድርጅቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

·        ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች በሚዘጋጀው የጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።

 

በስልክ ቁጥር 046 220 1752/2285/2117

 

የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት

ሀዋሳ

Save Tender