በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለሰራተኞቹ የደንብ ልብስ የስራ ሴፍቲ አልባሳት እና ጫማዎች በሚፈለገው በጥራትና በብቃት አምርቶ/ሰርቶ ለማቅረብ ልምድ፡ብቃት. ችሎታና ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ፡-
የጨረታ ማስታወቂያ ቁፕር
ኬኢኮአመኬፋ 009/2018
በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለሰራተኞቹ የደንብ ልብስ የስራ ሴፍቲ አልባሳት እና ጫማዎች በሚፈለገው በጥራትና በብቃት አምርቶ/ሰርቶ ለማቅረብ ልምድ፡ብቃት. ችሎታና ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ፡-
1. ነጭ ገዋን በቴትረን 6000/ተመሳሳይ ጨርቅ ብዛት 140
2.ገዋን በቴትረን 6000/ተመሳሳይ ጨርቅ ብዛት 56
3. ቱታ በቴትረን 6000/ተመሳሳይ ጨርቅ ብዛት 66
4.ሸሚዝና ሱሪ በቴትረን 6000/ተመሳሳይ ጨርቅ ብዛት 332
5.ኮትና ሱሪ በቴትረን 6000/ተመሳሳይ ጨርቅ ብዛት 90
6.የወንዶች ሸሚዝ ብዛት 104
7. ካኪ ቱታ ብዛት 200
8. የወንዶች ቆዳ ጫማ/በት/ ብዛት 169
9. የወንዶች አጭር ቆዳ ጫማ ብዛት 226
10. የሴቶች ቆዳ ጫማ አይነት 1 ብዛት 48
11. የሴቶች ቆዳ ጫማ አይነት 2 ብዛት 31
12. የወንዶች ፕላስቲከ ቦት ጫማ ብዛት 70
13. የወንድና የሴት ሴፍቲ ጫማ ብዛት 172 + 18
14. የተለያዩ ግላቮች እና የሴፍቲ እቃዎች ብዛታቸው በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር የተቀመጡትን
ከሀገር ውስጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም -
1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የ/2018 ዓ.ም/ ግብር የከፈሉ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ ታከስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ጨረታውን መሣተፍ ይችላሉ ፣
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት እና ከአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ከግዥ ክፍል ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ መግዛት ይችላሉ፣
3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው፣
4. ተጫራቾች እያንዳንዱን ናሙና ከቴከኒካል አፈርና ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 3 የተገለጹትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ፣ ከዚህ በተጨማሪ ፋይናንሻል ኦፈር ለብቻ በአንድ ፖስታ ታሽገው አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ የግዥ የስራ ሂደት ቢሮ እስከ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሰነዶቹን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው በዚሁ እለት በ4፡00 ይዘጋል፡፡
5. ጨረታው ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ቴክኒካል አፈሩ ብቻ በ4፡30 በአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡የተጫራቶች አለመገኘት ጨረታውን መክፈት አያግደም፡፡ቴክኒካል ምዘና/ናሙና ፍተሻ በድርጅቱ በራሱ ይከናወናል፡፡
6. እያንዳንዱ ናሙና ተፈትሾ ቴከኒካል ምዘና ያለፉት ተጫራቾች ብቻ ፋይናንሻል ኦፈራቸው ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡ 0ዐ ሰዓት በአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መከፈት አያግደም፡፡
7. እዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ:ስልክ ቁጥር 011554 57 71/0920935336
በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ
