ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የተለያዩ ያገለገሉ የግንባታ፣ የመደበኛ፤ የሳኒተሪ፣ የኤሌክትሪክ፣ የኤሌከትሮኒክስ፣ ቁርጥራጭ ብረቶች፤ የማሽንና ተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ጎማና ባትሪ እና የፈርኒቸር እቃዎችን ባህርዳር ዋናው ቢሮ በሚገኙ መጋዝኖች ባህር ዳርና አካባቢው በሚገኙ ፕሮጀከቶች እና ጎንደር ከሚገኘው ከፍ/ፍ/ቤት መጋዘን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ግስጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የተለያዩ ያገለገሉ የግንባታ፣ የመደበኛ፤ የሳኒተሪ፣ የኤሌክትሪክ፣ የኤሌከትሮኒክስ፣ ቁርጥራጭ ብረቶች፤ የማሽንና ተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ጎማና ባትሪ እና የፈርኒቸር እቃዎችን ባህርዳር ዋናው ቢሮ በሚገኙ መጋዝኖች ባህር ዳርና አካባቢው በሚገኙ ፕሮጀከቶች እና ጎንደር ከሚገኘው ከፍ/ፍ/ቤት መጋዘን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ዕቃዎቹ ያሉበትን ሁኔታና አይነታቸውን በአካል ተገኝቶ መመልከት ይቻላል። በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ተወዳዳሪዎች፡-
1. የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው፣
2. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም /unconditional bank guarantee/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
3. የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ የድሮው አማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የአሁኑ የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/በመከፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. የጨረታ መዝጊያ እና መከፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናት በመቁጠር) ብቻ ባ/ዳር ከተማ በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ወደ ዲያስፖራ በሚወስደዉ መንገድ በሚገኘው የድርጅቱ ህንፃ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው በ15ኛው ቀን በተገለጸዉ ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ የመዝጊያና መከፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚያኑ ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡
6. ዝርዝር የጨረታ መመሪያውን እና የውል ይዘቱን እንዲሁም የሚሸጡ ዕቃዎችን ዝርዝርበሙሉ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሙላት አለበት፡፡
7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 05-82-18-10-04/0912783066/0918715641/
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
