Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
  • Address , Phone: +251911984467
  • Website
  • Deadline23 Jun 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2026-06-23 10:00:00
  • Categories Printing And Publishing

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የህትመት ዓይነቶችን ለማሳተም ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) መሰረት የህትመት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የተለያዩ ህትመቶችን ለማሳተም የወጣ የጨረታ

ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/18/2018

 

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የህትመት ዓይነቶችን ለማሳተም ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) መሰረት የህትመት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ፈቃድ፣ ቫት ተመዝጋቢነት፣ ቲን፣ EGP (የአቅራቢ ተመዝጋቢነት) እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ ኤማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ዶክመንት መሰረት ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ከኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ጋር እንዲሁም ፋይናንሽያል በተለያዩ ፖስታ በማድረግ ፋይናንሽያል ሰነዱ ዋና እና ኮፒ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ዋጋ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል። ጨረታው ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ሥነሥርዓት ይከናወናል። ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፣ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ስልክ ቁጥር+251911984467 ወይም +251910567578

ፋክስ፡-0114-421312

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Save Tender