Tender Detail

Tender Details


ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት የፅዳት አገልግሎት ግዥ ግልፅ ጨረታ ለማዕከሉና ለመስቀል አደባባይ ፋስሊቲ ማኔጅመንት ለቢሮ ፣ የተሸከርካሪ ማቆሚያ ፓርኪንግ እና ፕላዛ ላይ የፅዳት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል፡፡


በድጋሚ የወጣ የፅዳት አገልግሎ ግዥ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ 023/2018     

ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት የፅዳት አገልግሎት ግዥ ግልፅ ጨረታ ለማዕከሉና ለመስቀል አደባባይ ፋስሊቲ ማኔጅመንት ለቢሮ ፣ የተሸከርካሪ ማቆሚያ ፓርኪንግ እና ፕላዛ ላይ የፅዳት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማራና ከድርጅታችን ጋር በማንኛውም ሥራ ውል ፈጽሞ እየሰራ ያልሆነ፣
  2. ከማንኛውም ዕዳና ዕገዳ ነፃ የሆነ ድርጅት ፣
  3. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምሰክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ከሰኔ 07 ቀን 2018 ዓ.ም ለ8 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ 9 ኛው ቀን ሰኔ 8  ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት 8፡35 ሰዓት የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ብር 500/አምስት መቶ/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ብር 100,000.00(መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸዉን እና የጨረታ ማስከበሪያዉን በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለማዕከሉና ለመስቀል አደባባይ ፋስሊቲ ማኔጅመንት ለየብቻ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  8. ይህ ጨረታ በድርጅቱ የግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  9. የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ 3 ቀናት ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 10% የዉል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን መስቀል አደባባይ በሚገኘው የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  12. ማሳሰቢያ፡-የፋይናንስ ውድድሩ ለማዕከሉና ለመስቀል አደባባይ ፋስሊቲ ማኔጅመንት ለየብቻ በሚቀርብ ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ  በሚሞሉት መሰረት ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 0115151693 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት

Save Tender