Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Management Institute (EMI) (የኢትዮጵያ ብቃትና ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት)
  • Address የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ከመገናኛ አያት 49 መንገድ ከሰዓሊተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0994115513
  • Website
  • Deadline29 Jun 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2026-06-29 10:30:00
  • Categories Used Items

የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 014/18

 

የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1.     በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2.     ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከሰኞ እስከ ዓርብ 2 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው /ቤት 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ፍል በመፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 ከአቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

3.     ንብረቶችን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ አዲስ አበባ ዋና ግቢ እና ደብረዘይት ሥልጠና ማዕከል በመገኘት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማየት ይችላሉ፡፡

4.     ተጫራቾች የሚገዙትን ልዩ ልዩ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በኢንስቲትዩቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

5.     ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይውል እና 16ኛው ቀን 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 430 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡

6.     የጨረታው ፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት ያስተጓጉልም፡፡

7.     የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው

8.     ልዩ ልዩ ንብረቶች የመነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

9.     ኢንስቲትዩቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡

10. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ በመከፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መከፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኢንስቲትዩቱ ገቢ ይደረጋል

11. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንዳስፈላጊቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

አድራሻ፡ አዲስ አበባ የካ ፍለ ከተማ ወረዳ 03 ስል ቁጥር 0116-454147/0116-453598 /0118-694931 ከሳሊህተ ምህረት ማርያም /ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ሕንፃ

 

የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት

Save Tender