ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ የሚገኘውን የድርጅቱ ይዞታ (መርሃ ጥበብ ቅርንጫፍ መ/ቤት) ለንግድ አገልግሎቶች ማለትም ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለሱቆች ወዘተ ስራዎች ሲጠቀሙ ለሚችሉ ድርጅቶች ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድር ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 017/18
ድርጅታችን ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ የሚገኘውን የድርጅቱ ይዞታ (መርሃ ጥበብ ቅርንጫፍ መ/ቤት) ለንግድ አገልግሎቶች ማለትም ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለሱቆች ወዘተ ስራዎች ሲጠቀሙ ለሚችሉ ድርጅቶች ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድር ለማከራየት ይፈልጋል፡፡ ለዚህም የአካባቢውን የኮሪደር ልማትና የውጪ ገፅታ በጠበቀ ሁኔታ እንዲሁም ከቅርስ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የእድሳት ሂደቶች በመከተል በሚፈለገው መልኩ አስተካከሎ የተለያዩ የንግድ ስራዎችን መስራት ይቻላል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመስስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሺያል እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው::
ጨረታው 30/10/ ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በገዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ ገፅ (www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise,
አዲስ አበባ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
