የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት አዲስ አበባ ክላስተር ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን እና አገልግሎት የማይሰጡ አዳዲስ የኮፒውተር ቀለሞች ባሉበት ሁኔታና ቦታ ለጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች ሽያጭ የጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር (አ/አ02/10/7621/18)
የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት አዲስ አበባ ክላስተር ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን እና አገልግሎት የማይሰጡ አዳዲስ የኮፒውተር ቀለሞች ባሉበት ሁኔታና ቦታ ለጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቶች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት አዲስ አበባ ከለላስተር፣ ስቶር ውስጥ በሚገኘው በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የ ተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለልዩ ልዩ ንብረቶችን ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚገዙትን ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሽ ኤንቨሎፕ በማድረግ የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት አዲስ አበባ ክላስተር ጠቅላላ አገልግሎት ባልቻ ሆስፒታል አጠገብ ደማ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 805 ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፣
6. ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን የመነሻ ዋጋ 10 (10%) ያልያስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራቾች ከጨረታ ውድቅ ይደረጋል፡፡
7. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸውን በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ገደብ መክፈል ይኖርባቸዋል፡ ፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻለ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
10. አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0921127523/0922934313 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
12. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን 10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለበቸው።
13. አገልግሎት ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማኛውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ የጤና መድን አገልግሎት
አዲስ አበባ ክላስተር ጽ/ቤት
