Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Address በምስራቅ ሸዋ ዞን ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462 -114-616
  • Website
  • Deadline01 Jul 2026, 2:00 PM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-07-01 14:30:00
  • Categories Petroleum Products Fuel, Diesel , Oil And Lubricant

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2018 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ ተሽከርካሪዎችና መሣሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ ዓይነት ያላቸው ዘይቶችና ቅባቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢመአ/ሻሸ/097/2018


በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት 2018 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ ተሽከርካሪዎችና መሣሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ ዓይነት ያላቸው ዘይቶችና ቅባቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠብቅባቸዋል፡፡

1.
ተጫራቾች 2018 . የታደሰ ንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡

2.
ተጫራቾች 2017 በጀት ዓመት ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ ከሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡

3.
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 50,000.00(ሀምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልከ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

4.
ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴከኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በእለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5.
ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው 16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኃላ 800 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 830 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል። በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

6.
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ/በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000002579859 ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ዕቃ ግዥ///አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይቻላል።

7.
በጨረታው መከፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።

8.
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462-114-616 መጠቀም ይችላሉ።

9.
/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ

መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

Save Tender

ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (Raw Local Coal) ግዥ

READ MORE
ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (Raw Local Coal) መጠን 41,500 ቶን መግዛት

READ MORE