Tender Detail

Tender Details

  • Company Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
  • Address አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114420688
  • Websitehttp://www.mughercement.com.et/
  • Deadline01 Sep 2018, 9:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 575.00 ከነቫቱ
  • opening dateነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Categories Petroleum Products Fuel, Diesel , Oil And Lubricant

ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (Raw Local Coal) ግዥ


ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/24/2018

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (Raw Local Coal) መጠን 41,500 (አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ) ቶን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፣ በጨረታ የሚሳተፉ ድርጅቶች በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾች ወይም አቅራቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ያላቸው፤ አምራች ከሆናችሁ ከከልል መንግሥት የተሰጠ የማዕድን ማምረት ሥራ ፍቃድ ሰርተፍኬት አቅራቢ ከሆኑ የአቅራቢነት ፍቃድ፤ የ2018 ዓ/ም የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የታከስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ምርመራ ውጤት እና ይዞታ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ፤ (አስገዳጅ መስፈርት ሲሆኑ አሟልቶ ያላቀረበ ከጨረታ ይሰረዛል) የተጠቀሱትን ማስረጃዎች (ንግድ ምዝገባ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስና የታከስ ከፋይ ምዝገባ ኮፒ) በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ገርጂ አካባቢ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል መዳረሻ ወለል ከሚገኘው የፋብሪካው ግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው በዕለቱ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ

✨ messages.ai_summary
- Procurement: Unwashed local coal (Raw Local Coal) — 41,500 tons — for Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory, Addis Ababa. - Deadline: Submission by 26 Nehase 2018 E.C., 3:30 AM; bid opening same day at 4:00 AM. - Bid document price: ETB 575.00 including VAT. Bid bond: ETB 2,000,000.00 via bank certified cheque (CPO) or unconditional bank guarantee. - Mandatory eligibility: renewed trade license and commercial registration, manufacturer or supplier permit in the sector (mining license from regional government for manufacturers; supplier license for suppliers), paid 2018 E.C. current-year tax, VAT and taxpayer registration, and geological survey result with holding statement. Failure to provide these leads to disqualification.
Save Tender

ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (Raw Local Coal) መጠን 41,500 ቶን መግዛት

READ MORE
ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (Raw Local Coal) ግዥ

READ MORE