Tender Detail

Tender Details

  • Company Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
  • Address ዋናው መስሪያ ቤት አራት ኪሎ አዲስ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ, Phone: 0111555230
  • Websitehttps://ethbspe.org/en_US/
  • Deadline07 Jul 2026, 2:00 PM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2026-07-07 14:30:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

ድርጅታችን ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ የሚገኘውን የድርጅቱ ይዞታ (መርሃ ጥበብ ቅርንጫፍ መ/ቤት) ለንግድ አገልግሎቶች ማለትም ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለሱቆች ወዘተ ስራዎች ሲጠቀሙ ለሚችሉ ድርጅቶች ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድር ለማከራየት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 017/18



ድርጅታችን ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ የሚገኘውን የድርጅቱ ይዞታ (መርሃ ጥበብ ቅርንጫፍ መ/ቤት) ለንግድ አገልግሎቶች ማለትም ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለሱቆች ወዘተ ስራዎች ሲጠቀሙ ለሚችሉ ድርጅቶች ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድር ለማከራየት ይፈልጋል፡፡ ለዚህም የአካባቢውን የኮሪደር ልማትና የውጪ ገፅታ በጠበቀ ሁኔታ እንዲሁም ከቅርስ ጋርተያያዥነት ያላቸውን የእድሳት ሂደቶች በመከተል በሚፈለገው መልኩ አስተካከሎ የተለያዩ የንግድ ስራዎችን መስራት ይቻላል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክርወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታከስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመስስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሺያል እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ስጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው::

ጨረታው 30/10/ ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴከኒካል መጫረቻ ሰነድ ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በገዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴከኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡



ስስክ ቁጥር 011-1-55-52-30

ድረ ገጽ 78 (www.ethbspe.org)

Berhanena selam printing enterprise,


አዲስ አበባ

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

Save Tender