Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Trading Businesses Corporation (የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን)
  • Address ደብረዘይት መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114 43 12 76
  • Websitehttps://www.etbc.com.et/index.php/home
  • Deadline24 Jun 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price700.00
  • opening date2026-06-24 10:30:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ንፋስ ስልክ ላ/ክ/ከተማ ካዲስኮ አካባቢ የሚገኘውን እና ቀደሞ ለግዥ ማማከር ንግድ ስራ ዘርፍ ለቢሮ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን ባለ 2 ወለል (G+2) ህንፃ ባለበት ሁኔታ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በየሁለት ዓመቱ በሚታደስ ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡


በድጋሚ የወጣ የሕንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ንፋስ ስልክ //ከተማ ካዲስኮ አካባቢ የሚገኘውን እና ቀደሞ ለግዥ ማማከር ንግድ ስራ ዘርፍ ለቢሮ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን ባለ 2 ወለል (G+2) ህንፃ ባለበት ሁኔታ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች በየሁለት ዓመቱ በሚታደስ ውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሎት 15 (አስር አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

1.     አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤

2.     የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 /ሰባት መቶ ብር/ በመክፈል ከሰኔ 3 ቀን 2018 . እስከ ሰኔ 17 ቀን 2018 . ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 230 እስከ ቀኑ 630 እንዲሁም ከሰዓት ከቀኑ 730 እስከ 1130 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 230 እስከ ቀኑ 630 በቅሎ ቤት ከሚገኘው የኮርፖሬሽኑ //ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መግዛት ይችላሉ፤

3.     ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ህንፃው የሚገኝበት ቦታ በአካል ቀርበው መመልከት ይችላሉ፤

4.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ሰኔ 17 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 430 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

5.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በሲ.. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፤

6.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ በግልጽ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ማሳየት አለባቸው፤

7.     ጨረታው ሰኔ 17 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 4:30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው /ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፣

8.     ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዳቸው የድርጅታቸውን ስም፣ ፊርማ እና ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፤ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው የተጫራቹን አጭር ፊርማ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤

9.     ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሰጡትን ዋጋ መለወጥም ሆነ ማሻሻል አይችሉም፤

10. የጨረታው አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነታቸው በተገለፀ 10 /አሥር/ የሥራ ቀናት ውስጥ በመቅረብ ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልተዋዋሉ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ተወርሶ ኮርፖሬሽኑ ሌላ አማራጭ የሚወስድ ይሆናል፤

11. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

12. ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 014-16-34-83 መጠየቅ ይቻላል

 

አድራሻ፡- በቅሎ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር፡- 0114-16-34-83 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

 

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Save Tender