Tender Detail

Tender Details


ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር ዋና መሥሪያ ቤት የሚገኙ ፤ያገለገሉ እና አዲስ የትራከተር ጎማዎች የቀላል መኪና አዲስ እና አሮጌ ጎማዎች እና ቸርኬዎች ፣ የፎርድ መኪና የተቀየሩ የቦዲ ዕቃዎች: ያገለገሉ በርሜሎች ፣ ያገለገሉ ባትሪዎች ፣ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

- ኩባንያችን ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር ዋና መሥሪያ ቤት የሚገኙ ፤ያገለገሉ እና አዲስ የትራከተር ጎማዎች የቀላል መኪና አዲስ እና አሮጌ ጎማዎች እና ቸርኬዎች የፎርድ መኪና የተቀየሩ የቦዲ ዕቃዎች: ያገለገሉ በርሜሎች ያገለገሉ ባትሪዎች ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ የወጣ ጨረታ ማስተወቂያ

ኩባንያችን ሪዬስ ኢንጂንሪንግ በዋና መሥሪያ ቤት የሚገኙ ያገለገሉ እና አዲስ የትራከተር የከባድ የቀላል መኪና ጎማዎች ቼርኬዎች የፎርድ መኪና የተቀየሩ የቦዲ ዕቃዎች ያገለገሉ በርሚሎች ያገለገሉ ባትሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) ከፍሎ በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ንብረቶቹን ሣሪስ ዋናው መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር ከጠዋቱ 3:00 እስከ 11:00 ሰአት ድረስ በአካል ተገኝተው ማመልከት ይችላል።

- ተጫራቾች የሚፈልጉትን ንብረት ለጨረታው ሲባል በተሰጣቸው ካታጎሪ መሠረት ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ጋር በመጨመር ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ፎርም ላይ ብቻ በመሙላት ለጨረታ ማስከበሪያ ያቀረቡትን ዋጋ በጅምላ 100 ሺህ ብር CPO በማስያዝ የድርጅታችን ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በሚኖረው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ

1.     የጨረታ አሸናፈው በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመከፈል ዕቃዎችን ማንሳት አለባቸው።

2.     በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከፍያ ፈጽመው ዕቃዎችን የማያነሱ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ወደ ድርጅቱ ገቢ ይደረጋል፡፡

3.     የጨረታ ተሸናፊዎች የአሸናፊዎች ዝርዝር ከተገለጸባቸው ቀን ጀምሮ ለጨረታ ያስያዙት ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

 

4.     በአንደኛው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

5.     የማንሻ ማሸን፣ መኪና፣ ጉልበት ሠራተኛ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያቀርባል።

6.     ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ስልክ ቁትር 0114-421133 የዉስትጥ መስመር-212 ወይም 208 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ አዲስ አበባ ደብረ ዘይት መንገድ (ሣሪስ ስካባቢ)

ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1116

አዲስ አበባ

 

ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክስዮን ማኅበር

Save Tender