የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሕግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በቀን 17/10/2018 ዓ/ም እና 20/10/2016 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሕግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በቀን 17/10/2018 ዓ/ም እና 20/10/2016 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት በተጫራች ስም የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝርመስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን እቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት ፡ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት፡እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣልዎት የምትፈልጉት የእቃ ሳሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልከ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት እንዲመጣልዎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የጨረታ መስፈርቶች፡-
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልግ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ
|
የጨረታ ቦታ |
የጨረታ ዓይነት |
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች |
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያና መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ቃሊቲ ጉምሩክ |
ግልፅ እና ሃራጅ |
ጫማዎች፣አልባሳት፡ ኮስሞቲክስ፡የመኪናመለዋጫ፡ ኤሌክትሪከእቃዎች፣ ተሽከርካሪመኪናዎች፣የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፡ምግብ ነክ፣እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች |
ለግልጽ ጨረታ እስከ 17/10/18 ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡45 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 4፡45 |
ለግልጽ ጨረታ እስከ 17/10/18 እና 20/10/2018 ከጠዋቱ 3፡45 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 5፡00 |
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘውትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀን 17/10/2018 ዓ/ም እና 20/10/2018 ባሉት ቀናት ግልፅ እስከ ጠዋቱ 3፡45 እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ ረፋዱ 5፡00 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በአካል በመገኘት በግዞት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር / በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ፡፡
3. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5% እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ ለሚ ወደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንከ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4 ተጨራቾች በሚከተለውየጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡
5. የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡በቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል::
6, ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ 3 የሥራ ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውሰጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ሰርትፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ከሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅሰቃሴያቸውን ለታከስ ማዕከሉ ያሳወቁበት፣ በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምሰከር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
8. ከላይ በተ.ቁ 7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ - ለተጨማሪ መረጃ በሰልክ ቁጥር፡- 022-224-1402 ደውለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት
