ዘመን ባንክ አ.ማ. ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን (የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ የቢሮ መገልገያ ኢኩፕመንቶች፣ ኮምፒዩተሮችና ተዛማጅ ዕቃዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የብረትና አልሙኒያም ቁርጥራጮች) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ያገለገሉ ንብረቶች እና ሌሎች ዕቃዎች ሽያጭ
ጨረታ ማስታወቂያ
ዘመን ባንክ አ.ማ. ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን (የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ የቢሮ መገልገያ ኢኩፕመንቶች፣ ኮምፒዩተሮችና ተዛማጅ ዕቃዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የብረትና አልሙኒያም ቁርጥራጮች) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ደንቦች፡-
1. ንብረቶቹን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት “ጎፋ መብራት ኃይል ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ት/ቤት “አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ፤ ወይም በስልክ ቁጥር 0115-57-58-25/011 668 78 09 በመደወል ወይም ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው በባንኩ ዋናው መሥሪያ ቤት 12ኛ ፎቅ ላይ በንብረት እና ሎጂስቲክ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፣
2. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና የዋጋ መሙያ ቅጽ ከባንኩ የንብረት አስተዳደርና ሎጂስቲክስ መምሪያ በመግዛትና እና በመሙላት በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች በምድብ (ሎት) ተለይተው ከተቀመጡት ንብረቶች የመረጡትን ለመግዛት የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከቀኑ 11፡00 ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንጻ 12ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
4. ጨረታው ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 03፡30 ሰዓት በባንኩ ሕንጻ 19ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
5. ጨረታው በሚካሄድበት ዕለትና ሰዓት መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው፡፡
6. አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ክፍያ መፈጸም አለበት። ይህን ባያደርግ ግን ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
7. የጨረታ አሸናፊው ንብረቶቹን ከማስተካከል፤ ከመጫንና ከማጓጓዝ ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ክፍያ ገዢው ይከፍላል።
8. ተጨማሪ የጨረታ ደንቦች የጨረታ ሰነድና የዋጋ መሙያው ቅጽ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ዘመን ባንክ አ.ማ
