Tender Detail

Tender Details

  • Company Tracon Trading Plc
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline07 Jul 2026, 5:34 PM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-06-14 17:33:00
  • Categories Software & Applications Development

ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ ማህበር ለፋብሪካዎቹ ከጥሬ ዕቃ አቀባበል (Raw Material Receiving) ጀምሮ እስከ ማምረቻ ክፍሎች እና የተጠናቀቁ ምርቶች ክምችት ድረስ ያለውን የስራ ፍሰት ያማከለ፤ ግልጽ እና ዘመናዊ የድርጅት መዋቅር (organizational Chart) መዘርጋት የሚችል ባለሙያ ወይም አማካሪ ድርጅት አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ 07/10/2018

ድርጅታችን ትራኮን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ ማህበር ከቀድሞ የንግድ ሥራዎቹ በተጨማሪ  ከፍተኛ ጥራት ያላቸው አራት ማዕዘን (RHS) ካሬ (SHS) እና ክብ የብረት ቱቦዎችን (Tubular Steel) ለኮንስትራክሽን እና ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት የሚያመርት ዘመናዊ የብረት ፋብሪካ አቋቁሞ ይገኛል በተጨማሪ ድርጅታችን የተለያዩ የምስማር ምርቶዎችን በማምረት ለገበያ ያቀርባል፤ከዚህም በላይ በአሁኑ ወቅት የአርማታ ብረት ፋብሪካ ለመገንባት የመጨረሻ ሂደት ላይ ይገኛል፤ አሁን ላይ ድርጅታችን ስራውን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ እና የስራ ክፍሎችን በግልፅ ለመለየት ይረዳው ዘንድ ደረጃውን የጠበቀ የድርጅት መዋቅር መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ስለሆነም ለፋብሪካዎቹ ከጥሬ ዕቃ አቀባበል (Raw Material Receiving) ጀምሮ እስከ ማምረቻ ክፍሎች እና የተጠናቀቁ ምርቶች ክምችት ድረስ ያለውን የስራ ፍሰት ያማከለ፤ ግልጽ እና ዘመናዊ የድርጅት መዋቅር (organizational Chart) መዘርጋት የሚችል ባለሙያ ወይም አማካሪ ድርጅት አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

ከአማካሪው የሚጠበቁ ዋና ዋና ተግባራት

➢ የፋብሪካ መዋቅር ንድፍ (Complete organizational Chart) ከፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ (Plant Manager) ጀምሮ እስከ ማምረቻ መስመር ሰራተኞች እና ረዳቶች ድረስ ያለውን የሪፖርት አቀራረብ መስመር በግልጽ የሚያሳይ መዋቅር ማዘጋጀት፡፡

➢ የክፍሎች ዝርዝር መለያ (Departmental Mapping)፡-ዋና ዋና የሥራ ክፍሎችን መለየት፣ (ለምሳሌ- የምርት ክፍል፣ ጥራት ቁጥጥር/ላቦራቶሪ፣ የቴክኒክና ጥገና ክፍል፣ ደህንነትና አካባቢ ጥበቃ (EHS)፣ ግዢና ሎጂስቲክስ፣ እና የሰው ኃይል አስተዳደር)፡

➢ የስራ ዝርዝር መግለጫ እና መመዘኛ (Job description (JD) & Key performance indicators (KPls))፦ ለዋና ዋና የቴክኒክ ባለሙያዎች (ለምሳሌ፦ የቱቦ ማሽን ኦፕሬተሮች፣ የጥራት ቁጥጥር ባለሙያዎች፥ የጥገና መሐንዲሶች) ዝርዝር የሥራ መግለጫ እና የሥራ አፈጻጸም መገምገሚያ ማዘጋጀት፡፡

➢ የፈረቃ (Shift) አደረጃጀት ሥርዓት፦ ፋብሪካው በፈረቃ ለሚያደርገው የ24 ሰዓት የማምረት ሂደት ተስማሚ የሆነ የሰው ኃይል ስምሪት ዕቅድ ማውጣት፡፡

ተፈላጊ ችሎታና ማረጋገጫ፦

➢ በከባድ ኢንዱስትሪዎች፣ በተለይም በብረታ ብረት፤ በቱቦ ማምረቻ (Tube/Pipe Mill) ወይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የድርጅት መዋቅር በመዘርጋት ረገድ በቂ የሥራ ልምድ ያለው/ላት።

  • የማምረት ሂደትን እና የፋብሪካ ውስጥ ደህንነት (Safety) ህጎችን በሚገባ የሚረዳ/ምትረዳ፡፡

➢ ስራውን 40(አርባ) የስራ ቀናት ውስጥ አጠናቆ ማስረከብ የሚችል ወይም የምትችል፡፡

የማመልከቻ መመሪያ፦

ይህን ስራ ለመስራት ፍላጎት ያላችሁ የግል ባለሙያዎች ወይም አማካሪ ድርጅቶች፤ከዚህ ቀደም ሌሎች ድርጅቶች ወይም ፋብሪካዎች ላይ የሰራችሁበትን ተመሳሳይ የስራ (ማስረጃ) እና የዋጋ ማቅረቢያችሁን (Financial Proposal)በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ(Envelope) ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን እስከ ሰኔ ቀን 30 ድረስ በኢሜይል hrtracon@gmail.com ወይም በአካል ቸርችል ጎዳና ጥቁር አንበሳ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ትራኮን ታወር 1ኛ ፎቅ የአልሙኒየም ሽያጭ ቢሮ ወይንም ጀሞ 3 ወደ ሎጂ በሚወስደው መንገድ ትራኮን ቡና ቦርድ ዋና መስሪያ ቤት አስተዳደር ቢሮ 4ኛ ፎቅ በግንባር በመቅረብ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09-30-07-91-71 ወይም 0976624176

Save Tender