ሲዳማ ኤልቶ ኃ/የተወሰነ ኅ/ስራ ዩኒየን ለአሲዳማ አፈር ማከሚያ አገልግሎት የሚውል 16,000 ኩንታል ኖራ ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በማንሳት ወደ ተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች ማጓጓዝ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ሲዳማ ኤልቶ ኃ/የተወሰነ ኅ/ስራ ዩኒየን ለአሲዳማ አፈር ማከሚያ አገልግሎት የሚውል 16,000 ኩንታል ኖራ ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በማንሳት ወደ ተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች ማጓጓዝ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከድርጅቱ የማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መግለጫ ሰነድ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈለገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በአማካይ በኩንታል በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፈቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፡፡
2. ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
3. ከዚህ ቀደም በዘርፉ ተሰማርቶ ስራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ስራ አፈፃፀም ቢያንስ ሶስት ማቅረብ የሚችል፡፡
4. የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር ያመች ዘንድ በአንድ አካባቢ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም፡፡
5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈፀሙ በፊት ያሸነፉበትን ጭነት የማጓጓዣ ዋጋ 10 % በቅድሚያ ያስይዛል፡፡
7. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ቢያንስ 2000 ብር /ሁለት ሺህ ብር/ ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪናዎችን /የሰሌዳ ቁጥር፣ የሻንሲ ቁጥር ፣የመኪና ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አይይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ለሚጠፋው ንብረት በሙሉ ኃላፊነት የሚወስድ የጭነት ኢንሹራንስ /ካርጎ ኢንሹራንስ/ ያለውና መረጃውን ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኤንቬሎፕ በማሸግ በ 7ኛው ቀን ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
11. ጨረታው በ8ኛው ቀን /የስራ ቀን /ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ፅ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስቁ 0462124704 /0930108356 መደወል አልያም ፅ/ቤት ድረስ በአካል መቅረብ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፊት ለፊት
ሲዳማ ኤልቶ ኃ/የተወሰነ ኅ/ስራ ዩኒየን
