Tender Detail

Tender Details


በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ በፋብሪካው ዋና ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ብረታ ብረቶችን፣አንድ ደብል ካፕ ሚትሱቢሽ ተሽከርካሪ፣ሁለት የሲሚንቶ ወፍጮ ሴፓሬተሮችን፣ የውሃ ማጠራቀሚያ /ማከማቻ ታንከር/ማይዝግ ፣ያገለገሉ ጎማዎች ፣አንድ አዲስ የትራከተር ጎማ ፣የኬሚካል መከላከያ ሸከላዎችን፣የወረቀት ማሸጊያ ከረጢቶችንና የብረት ዝገት መከላከያ ቀለም እና ያገለገሉ ፍሪ


የሚወገዱ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር C002-2018


በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ በፋብሪካው ዋና ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ብረታ ብረቶችን፣አንድ ደብል ካፕ ሚትሱቢሽ ተሽከርካሪ፣ሁለት የሲሚንቶ ወፍጮ ሴፓሬተሮችን፣ የውሃ ማጠራቀሚያ /ማከማቻ ታንከር/ማይዝግ ፣ያገለገሉ ጎማዎች ፣አንድ አዲስ የትራከተር ጎማ ፣የኬሚካል መከላከያ ሸከላዎችን፣የወረቀት ማሸጊያ ከረጢቶችንና የብረት ዝገት መከላከያ ቀለም እና ያገለገሉ ፍሪጆችን እና የተለያዩ በጣውላ የተሰሩ ስብራባሪ ወንበሮችን ፣ጠረጴዛዎች እና መደርደሪያዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ፡፡ በመሆኑም _ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልቶ መወዳደር ይችላል፡፡

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የተጨማሪ እሴት ታከስ ሰርተፍኬት እና ለግብር ከፋይ የሚሰጥ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች ባቱ ከተማ ካለው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ከኩዌት ኤምባሲ 10 ሜትር ገባ ብሎ ናሚቢያ ወይንም ጅቡቲ ኤምባሲ ፊትለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር ሶስት መቶ (300.00) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድና የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ንብረቱ የሚገኝበት ባቱ(ዝዋይ) ከተማ ፋብሪካው ቅጥር ግቢ ድረስ በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 3 በመቶ(3%) በባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ ስም የተዘጋጀ የባንከ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡

5. ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት/ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይታሽጎ/ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይበተጠቀሰው አድራሻ አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ናሚቢያ/ጂቡቲ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ማርኬቲንግ ማስተባበሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻው ቀን በዓል ወይንም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

6. የጨረታው አሸናፊዎች ተለይቶ እንደታወቁ ያሸነፉበትን ዋጋ ቀርበው ከከፈሉ በኋላ በአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ በራሳቸው ተሽከርካሪ ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡፡

7. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ

አ.አ ስልክ ቁጥር 011-6-18-43-10/17

ባቱ ስልክ ቁጥር 046-441-34-15

ስ.ስ ፋክስ ቁጥር 011-618-15-29

ባቱ ፋክስ ቁጥር 046-441-24-63

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ

Save Tender