Tender Detail

Tender Details

  • Company Tsehay Insurance S.C (TISC) (ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ)
  • Address ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 25111111970
  • Websitehttps://tsehayinsurance.com/
  • Deadline06 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price197.00
  • opening date2026-07-06 10:30:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአሁኑ ቦታው (ቦሌ ድልድይ የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት) ከሚገኘው ቢሮ አዲስ ወዳስገነባው ዋና መ/ቤት አድራሻ (አዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊት ለፊት፣ ደጃዝማች ውቤ አካባቢ) ለማዛወር ይፈልጋል::


ፀሐይ ኢንሹራንስ ..

የጨረታ ማስታወቂያ፡

የቢሮ ዕቃ ማዛወር አገልግሎት ግዥ

 

ፀሐ ኢንሹራንስ . ዋና መሥሪያ ቤቱን በአሁኑ ቦታው (ቦሌ ድልድይ የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት) ከሚገኘው ቢሮ አዲስ ወዳስገነባው ዋና /ቤት አድራሻ (አዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊት ለፊት፣ ደጃዝማች ውቤ አካባቢ) ለማዛወር ይፈልጋል::

በዚሁ መሠረት፥ ኩባንያው የቢሮ ዕቃዎችን (ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮች፣ የኮምፒውተርና የሰርቨር ዕቃዎችን ወዘተ) እና የተለያዩ የኩባንያውን ሰነዶች በጥንቃቄ በማሸግ፣ በመጫን፣ በማጓጓዝ እና በማውረድ/በማደራጀት የተረጋገጠ ልምድ ያላቸውን ብቁ ድርጅቶች በዚህ ክፍት ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

ከተጫራቾች የሚጠየቁ መስፈርቶች፡

1.     ተጫራቾች ሀጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው::

2.     ተጫራቾች ተመሳሳይ ስራዎችን በመስራት 5 ዓመት ልምድ እና አቅም እንዳላቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::

3.     ተጫራቾች አስፈላጊ የሆኑ የማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን እና የማሸጊያ ቁሳቁሶችን የማቅረብ አቅም ሊኖራቸው ይገባል::

4.     ተጫራቾች ስራውን ለማጠናቀቅ የሚፈጅባቸውን ጊዜ የሚያሳይ የሥራ መርሃ ግብር ማቅረብ አለባቸው::

5.     የጨረታ ማስከበሪያ ተጫራቾች 50,000.00 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም ያለ ቅድመ ሁኔታ በሚፈጸም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ማቅረብ አለባቸው::

6.     አገልግሎት ሰጪው በእንቅስቃሴው ሂደት ለሚደርስ የሰነድ መጥፋት ወይም ጉዳት የኢንሹራንስ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅበታል::

የጨረታ ሂደት፡

·        የጨረታ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ድልድይ የቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው 3 ፎቅ የኩባንያው የፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ፣ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

·        የጨረታ ማስረከበሪያ፡ የተሟላ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሰኔ 29 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

·        የጨረታ መክፈቻ፡ ጨረታው ሰኔ 29 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

·        የኩባንያው መብት፡ ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

·  የቢሮቹን ጉብኝት፡ ተጫራቾች የሁለቱንም ሕንፃዎች አቀማመጥ እና የሚዛወሩ ዕቃዎችን አይነትና መጠን ለመገምገም የሚያስችል የቅድመ-ጨረታ የጉብኝት ፕሮግራም 22/10/2018 -28/10/2018 በስራ ሰዓት ማየት ይቻላል።

 

አድራሻ፡- ፀሐይ ኢንሹራንስ . ዋና መሥሪያ ቤት ቦሌ ድልድይ፣ የቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት

ስልክ፡- +251 111 119 70 / +251 116 50 66 30

Save Tender