ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለፁ የቢሮ መገልገያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
Ethio Life and General Insurance S.C
ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ
የጨረታ ቁጥር ELiG/04/2026
ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለፁ የቢሮ መገልገያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
|
ተ.ቁ |
ሎት |
አይነት |
መለያ |
|
1 |
ሎት 1 |
የቢሮ ዕቃዎች |
የሀላፊ ወንበር፣ የፀሀፊ ወንበር፤ ጠረጴዛ……ወዘተ |
|
2 |
ሎት 2 |
የፅህፈት ማሽኖች |
ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ |
|
3 |
ሎት 3 |
የህትመት ውጤቶችና ጥራዞች |
መመሪያዎች፣ ፖሊሲዎች፣ ወረቀቶችና ጥራዞች |
|
4 |
ሎት 4 |
የፅህፈት መገልገያዎች |
ፓንቸር፣ እስቴፕላር፣ ካኪ ወረቀቶች…ወዘተ |
በጨረታው ለመሳተፍ፡-
1. ተጫራቾች ከላይ ከተገለፁት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ በሁሉም ወይም በተናጠል መወዳደር ይችላሉ::
2. ተጫራቾች በመስኩ ሕጋዊ የንግድ ምዝገባ ስርተፊኬት፤ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን የግብር ግዴታቸውን የተወጡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት የብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ስም በሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
4. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት መስቀል ፍላወር በሚገኘው የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት “ሆም ኦፍ ሚሊዮንስ" ህንፃ 5ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ ስለጨረታው የሚገልፀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
6. ጨረታው በዚሁ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ በኩባንያው የስልጠና አዳርሽ 8ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል::
7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-4702077/0115570606 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
8. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት
መስቀል ፍላወር ሆምስ ኦፍ ሚሊዮንስ ሕንፃ 8ኛ ፎቅ
ስልክ 011-4702077/0115570606
