በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ጉሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር :- LP/OT/001/0KSF1&3/2018
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት ሶስት አርቲኩሌትድ ትራከተር ኪራያ የአገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ስነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ /አዲስ የንግድ ፈቃድ ፤የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክርወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን/መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ መረጃ ማቅረብ አለባቸው ::
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10:30) እና ቅዳሜ ከሰአት በፊት ከ2:30-6፡00 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ጉሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ
ግዥ ቡድን (ማስተባበር ቢሮ) አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራኒዮ፣
ከጦር ኃይሎች ወደ ዘነብ ወርቅ በሚወስደው መንገድ በተስምዶ 3 ቁጥር ማዞርያ / ቶታል ገባ ብሎ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ
ሕ - B ቢሮ ቁጥር 1371/125 ፎቅ፡፡
የስልክ ቁጥር (አድራሻ)+251-963442882/+251-916170834
አዲስ አበባ
መዝጊያ ቀን ድረስ 7:00-10:30 እና ገዝተው በጨረታው
3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሶስት አርቲኩሌትድ ትራከተር ኪራያ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታው መከፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው 17/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 17/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
5. ጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው ::
6. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ለ 60 ቀናት ነው፡፡
7.ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ
1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት
