የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅታችን ለህትመት ሥራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የህትመት ግብዓቶች ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው አምራች እና አከፋፋይ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋያ ድርጅት
የተለያዩ የህትመት ግብዓቶች ግዥ ገልጽ ጨረታ ቁጥር EMPDE/NCB/01/2018
ድርጅታችን ለህትመት ሥራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የህትመት ግብዓቶች ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው አምራች እና አከፋፋይ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ነጥቦች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
1. በዘርፉ ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ፤ የተ.እ.ታ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢ ምዝገባ ሰርተፍኬት መሆኑን።
2. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ማከ/ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችለሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ጨረታው ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
5. ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግደታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የድርጅቱ አድራሻ፡- ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ከሆሊ ሲቲ ሴንተር ህንጻ ሲደርሱ ወደ ቀኝ ታጥፎ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ ፡-011 646-3481 መረጃ ማግኘት ይቻላሉ።
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት
