በቂርቆስ ከፈለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት አመት ከ1ኛ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ::
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ከፈለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት አመት ከ1ኛ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
1ኛ. አላቂ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የጓሮ አትከልት ዘር ግዥ፣ የመኪና ዲኮር እቃዎች ግዥ
2ኛ. የአመት ውል፡- የቢሮ ማሽን ጥገና (ኮምፒዩተር፤ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ሰርቪስና ጥገና)፤የህዝብና የእቃ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የቢሮ እድሳትና ጥገና የህትመት ስራ፤የዲጄና ዲኮር አቅርቦት፤የቢሮ ፈርኒቸሮች ጥገና፣የጉልበት ስራ እገልግሎት የ90 ቀን ዶሮ እና መኖ ግዥ ፤ የዶሮ ኬጅ ግዥ፤የሰራተኛ ካፌ አገልግሎትና መስተንግዶ አቅርቦት፤ጀነሬተር ሰርቪስ ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. ተጫራቾች የዘመኑን የ2018 ዓ.ም የመንግስት ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
2. የቫት ተመዝጋቢና ህጋዊ የአቅራቢነት ማስረጃ ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በየሎቱ በመክፈል የጨረታ ሰነድ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ከፍል 6 ውስጥ የተገለጹትን እቃዎች ዝርዝር ዋጋቸውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በቂ/ከ/ከተማ ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚህ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር
ሎት1. የደንብ ልብስ 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት2. የፅዳት እቃዎች 20,000.00(ሀያ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት3. አላቂ የቢሮ እቃዎች 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት4. ቋሚ የቢሮ እቃዎች 35.000.00 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት 5. ህትመት ስራ ፤የሰራተኛ ካፌ አገልግሎትና መስተንግዶ፤ዲጄና ዲኮር አቅርቦት ፤ የሰውና እቃትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት 6. ጀነሬተር ሰርቪና ጥገና፤የቢሮ ፈርኒቸር ጥገናዎች፤የቢሮ እድሳትና ጥገና፤የቢሮ ማሽን ጥገናና ሰርቪስ፤የጉልበት ስራ አገልግሎት ብር 4,000.00 (አራት ሺህ ብር ብቻ) በባንክየተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት 7. የጓሮ አትከልት ዘር ግዥ ፤የዶሮ ኬጅ ግዥ፤የ90 ቀን ዶሮ እና መኖ ግዥ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ) በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና የማስገባት ግደታ አለባቸው፡፡
7. አሸናፊ ድርጅቶች በናሙናው/በስፔስፊኬሽኑ/ መሰረት ደረጃውን የጠበቀ እቃ የማስገባት ግደታ አለባቸው፡፡
8. ጨረታው በዘኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያኑ ቀን 4፡30 በፋ/ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ዘኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
9. መቅረብ ያለባቸው መረጃዎች፤- ቴከኒካል እና ፋይናንሻያል ሁለቱም ኦሪጅናልና ኮፒ ሲሆን ለየብቻቸው መታሸግ አለባቸው :: ነገር ግን ጨረታው ሲከፈት የሚከፈተው ኮፒው በመሆኑ ሲፒኦ (CPO) እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በሙሉ ኮፒው ውስጥ መደረግ አለባቸው፡፡በሁሉም ኤንቨሎፕ ላይ የደርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት፡፡
10. ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ድምር 10% የውል ማስከበሪያ ከውል በፊት ማስያዝ አለባቸው ፡፡የእያንዳዱ እቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ (ቫትን ጨምሮ) መቅረብ አለበት ይንን ያላደረጉ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናሉ፡፡
11. ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄዎች ወይንም መረጃ ማግኘት ለሚፈልጉ ስልከ ቀጥር0118883069 መጠቀም ይችላሉ፡፡
ስድራሻችን፡ ደ/ዘይት መንገድ ላንቻ ባቡር ፌርማታ በስተቀኝ 100 ሜትር ገባ ብሎ ቂርቆስ ከፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ማሳሰቢያ፡- ለሰራተኛ ካፌ አገልግሎት አስተዳደሩ የውሃ፣የመብራት እና የኪራይ አገልግሎት ከፍያ እራሱ ይሸፍናል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በቂርቆስ ክፈስ ከተማ ወረዳ4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
