Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የፅሕፈት መሣሪያዎችን፤ የፅዳት እቃዎችን፤ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን እንዲሁም የኤለክትሮኒከስ እቃዎችንና የሠራተኞች የደንብ ልብስ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የፅሕፈት መሣሪያዎችን፤ የፅዳት እቃዎችን፤ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን እንዲሁም የኤለክትሮኒከስ እቃዎችንና የሠራተኞች የደንብ ልብስ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ አቅራቢዎች የጨረታው ሰነድ በአንድ ላይ ተያይዞ ስለሚገኝ በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያላችሁና በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑንእንገልፃለን።

ስለዚህ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉና በአቅርቦት የተመዘገበበትን የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የቫት ቲኦቲ (TOT) ተመዝጋቢዎች የሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ቼከ ወይም ሲፒአ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ የንግድ ድርጅቶች ወይም ግለሰብ ነጋዴ ይህ ጋዜጣ 17/11/2018 ዓ.ም ከወጣበት ቀን አንስቶ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11፡30 ጎሮ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል። ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15ኛው የሥራ ቀን እንዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በ4፡00 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ 4፡ 30 ላይ ይከፈታል። አቅራቢዎች የሚቀርቡት እቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆንና በሚያቀርቡት የጨረታው ሰነድ ላይ የድርጅቱን ስም አድራሻ ሕጋዊ ማኅተምና ፊርማ መስፈር አለበት። ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ከተጫራች የሚቀርበው ሰነድ የዕቃውን ዝርዝር ዓይነት ስምና የተመረተበት ሀገር /brade name/ እንዲሁም ዘመን የሚገልፅ ሆኖ የእቃው ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ ጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት።ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ኦሪጂናልና ኮፒውን ለይቶ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርጎ ማቅረብ አለባቸው። አሸናፊው በሚያቀርባቸው ዕቃ ላይ 10 % ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል። መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ማሳሰቢያ-፡ መ/ቤቱ የሚገኘው በጂማ መስመር ሆኖ በወሊሶ እና ወልቂጤ መሐል ከአ/አ 134ኪ. ሜርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ስልክ፤ on-345-01-17 ወይም 011-345-06-26


በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የጎሮ ወረዳ ፍርድ ቤት

Save Tender