የኢትዮጵያ ኤሌክትሪከ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ንአ/ግጨ-01/2019
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪከ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ
|
የሚወገደው ንብረት ዓይነት |
የሚገኝበት ቦታ |
መለኪያ
|
ብዛት
|
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ
|
የጨረታ መክፈቻ
|
|
1
|
50 ኬቪኤ 15 እና 33 ከሺ ትራንስፎርመሮች
|
ኮተቤ ኤሌክትሪካል ወርክ
|
በቁጥር
|
326
|
553,000
|
ነሃሴ05 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00
|
ነሃሴ05 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30
|
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቶች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደርይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡ ውድድሩ የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በአከሽን ኢትዮጵያ አከሲየን ማህበር በፈጠሩት የማወዳደሪያ ሲስተም መተግበሪያ auction.et መሰረት መሆኑን እየገለጽን፤ መስፈርቶቹ ከዚህ
እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
2. ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የኦከሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት
ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው::
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO)
ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና(Bid Security) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪከ አገልግሎት ስም ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት የአከሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡
6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የአከሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይ ስቶር(Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ፡፡
8. የጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ ከሚገለፅበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የእሸነፋችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ከፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት የመፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፣ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድርያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒአ ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል፡፡
9. ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ሊደረግ ይችላል፡፡
10. ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
11. የእከሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር
09-05-11-55-1 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
12. ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር on-1-11-98-97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሴክትሪክ አገልግሎት
