Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓ.ም 1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ የተለያዩ መድሀኒቶች እና አላቂ የህክምና ዕቃዎች ፣ የደንብ ልብስ ፤ ቋሚ እቃዎች ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች የተለያዩ ህትመቶች እና የጥገና እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ በ2019 ዓ.ም 1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ የተለያዩ መድሀኒቶች እና አላቂ የህክምና ዕቃዎች ፣ የደንብ ልብስ ፤ ቋሚ እቃዎች ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች የተለያዩ ህትመቶች እና የጥገና እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1.    ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤

2.    ንግድ ፍቃድ ያደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።

3.    ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢና አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት።

4.    ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 4ተኛ ፎቅ ቢ.ቁ 408 ዘወትር / በሥራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

5.    ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው።

6.    ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል ኦርጅናል ፣ ፋይናንሻል ኮፒ ፣ ቴክኒካል ኦርጂናል ማለትም ኮፒ የሆኑ ህጋዊ ሰነዶች ላይ ማህተም የተመታ ፣ ቴክኒካል ኮፒ እና የሚወዳደሩበትን አይነት በ4 ፖስታ ፋይናንሻል ኦርጂናል ፣ ፋይናንሻል ኮፒ፤ ቴክኒካል ኦርጂናል ፣ ቴክኒካል ኮፒ በፖስታው ላይ በመለየት ማህተም በመምታት እና በመፈረም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ/ ወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 408 በመገኘት ለዚህ በተዘጋጀው የተጫራቾች ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።

7.    ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የለሚ ኩራ/ክ/ከተማ ወረዳ 13 ራዕይ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 408 በኮሚቴዎች ይከፈታል።

8.    እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የተጫራቾች ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት እና ሙሉ ሰነዱን ሳይገነጠል መመለስ አለበት ይህን ያልተገበረ ተጫራች ውድቅ ይደረጋል።

9.    መ/ቤታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10.        ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ በመስሪያ ቤቱ ስም ሎት1 ፣ብር 25000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ፣ ሎት2 ፣ ብር 10000 (አስር ሺህ ብር) ፣ ሎት3 ፣ ብር 11000 (አስራ አንድ ሺህ ብር) ፣ ሎት4 ፣ብር 25000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ፣ ሎት5 ፣ ብር 12000 (አስራ ሁለት ሺህ ብር) ፣ ሎት6 ፣ ብር 13000 (አስራ ሶስት ሺህ ብር) ፣ ሎት7 ፣ ብር 45000 (አርባ አምስት ሺህ ብር) ለጥቃቅን ህጋዊ ደብዳቤ ከዚህ ውጪ የሚመጡ የጨረታ ማስከበሪያ አንቀበልም።

11.        ተጫራቾች በሰነዱ ላይ የተካተተውን መረጃ በሙሉ ሞልተው መላክ ይኖርባቸዋል።

12.        ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉትን ስራ 10% ለአሸነፉት ስራ የውል ማስከበሪያ የሚያስይዙ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።

13.        ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሳያሟላ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከርና ጨረታውን ለማሳሳትና ለማጭበርበር የሚሞክር ተጫራች ከጨረታ ይሰረዛል።

14.        ተጫራቾች ሣምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

15.        ማንኛውም ተጫራች cpo ቴክንካል ኦርጂናል ሰነድ ላይ አብሮ ማስገባት አለበት

አድራሻ - በአዲሱ የካራ መንገድ ከአቅም ግንባታ ጀርባ እና ወሰን ግሮሰሪ 200 ሜትር ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር – 0118 932 588 / 0118 932 255 / 0118 932 988

 

በለሚ ኩራ/ክ/ከተማ/ወረዳ 13 የራዕይ ጤና ጣቢያ

Save Tender