በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2/2018/2019
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ፡-
1. ሎት 1 የፅህፈት መሣሪያዎች
2. ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች
3. ሎት 3 የማሽን ቀለም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደርይችላሉ።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው፣
4. የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
5. የግዢው መጠን ከብር 500,000/አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሰውንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋርአያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፣ የአምራቹን ስም፣ የተመረተበትን ዓ.ም በዝርዝር ከዋናው ጨረታ ስነድጋር መያያዝ አለበት፣
8. ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለበት፤
9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለፅህፈት መሣሪያዎች ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር፣ ለተለያዩ ማሽን ቀለሞች ብር 50,000/ ሀምሳ ሺህ ብር/፣ ለዕዳት
ዕቃ 50,000/ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድቦንድ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10 ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 – 3 የተጠቀሱትን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በመከፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/የስራ ሂደት ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
11. ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጐ ይህ ማሰታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው ፣
12 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 8፡00 ድረስ የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለባቸው። በዛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ 8፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል።
13. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-3300112 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይመሆን እንዳለበት እንገልፃለን።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
