Tender Detail

Tender Details

  • Company ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር
  • Address ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 02/03 ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ , የቤት ቁጥር 184: አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115528874
  • Websitehttps://www.addismap.com/am/bole-advert
  • Deadline12 Aug 2026, 1:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-08-12 13:30:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Vehicle

ሜጋ ማተሚያ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር ያገለገሉ መኪኖችንና ሞተር ብስክሌቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


ያገስገሱ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡ሜማ/15/11/18

ኩባንያችን ሜጋ ማተሚያ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር ያገለገሉ መኪኖችንና ሞተር ብስክሌቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል፡፡

1. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ሜጋ ህንፃ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

2.  ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን በአካል በመቅረብ ገርጂ ሜታ አከባቢ በሚገኘው

የድርጅታችን መጋዝን በመገኘት መመልከት ይችላሉ:

3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6/02/2018 . ለዚህ ተብሎ በሜጋ ህንፃ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 217 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በስራ ስአት ማስገባት አለባቸው::

4. አንድ ተጫራች መግዛት የሚፈልገውን ከአንድ በላይ መኪና/ሞተር ብስክሌት ከሆነ ለሚጫረተው ለእያንዳንዱ መኪና/ሞተር ብስክሌት ዋጋ መጥቀስ አለበት::

5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት መኪና ሞተር ብስክሌት የሚጫረቱበትን አጠቃላይ ዋጋ ሃያ አምስት በመቶ (25%) በሜጋ ማተሚያ ኃላ.የተ.የግ. ስም በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ማዛዣ (ሲፒኦ) የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታው ስነድ ጋር ገቢ ማድረግ አለባቸው::

6. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒአ ጨረታውን ላላሸነፉት ብቻ የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ይመለስላቸዋል፡፡

7. የጨረታው አሸናፊዎች ቀሪውን ገንዘብ በአምስት (5) የሥራ ቀናት ውስጥ አጠቃለው ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ከፍለው ንብረቱን የማያነሱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅታችን ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡

8. ጨረታው 6/12/2018 . ከቀኑ 700 ተዘግቶ በእለቱ 6/12/2018 . ልክ ከቀኑ 7 30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሜጋ ህንፃ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር110 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታው ከመከፈት አያግደውም::

9. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሕጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ድራሻ፦ ቦሌ ሜጋ ህንፃ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 217

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 0913729631

 

ሜጋ ማተሚያ ኃሳፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር

 

Save Tender