Tender Detail

Tender Details

  • Company በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ
  • Address ደብረ ብርሃን ከተማ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251911388194
  • Website
  • Deadline06 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineEthiopian Herald
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-08-06 10:30:00
  • Categories Audit Service

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡-

1.    ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

2.    ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ብቻ በማሰራት ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

3.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት እስከ ቀኑ አስር ሠዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።

4.    ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኢንተርፕራይዙ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5.    ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓትና ቦታ በግልፅ ይከፈታል፡፡ ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል።

6.    ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።

7.    ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን /+251925750633/0913497204 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ

Save Tender