ላይፍ ጌት የበጎ አድራጎት ድርጅት 2017 እና የ2018 የሂሳብ ሰነድ በጨረታ አወዳድሮ በውጭ ኦዲት ማስመርመር ይፈልጋል::
የጨረታ ማስታወቂያ
ላይፍ ጌት የበጎ አድራጎት ድርጅት ከሃምሌ 27/2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፈዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊከ ማህበር ድርጅት ኤጀንሲ 0108 በምዝገባ ቁጥር ተመዝግቦ ፍቃድ የተሰጠው ድርጅት ነው:: ድርጅቱ 2017 እና የ2018 የሂሳብ ሰነድ በጨረታ አወዳድሮ በውጭ ኦዲት ማስመርመር ይፈልጋል::
በመሆኑም፦ የስራ ዘርፉ የሚመለከታችሁ የሂሳብ ባለሞያ ላይፍ ጌት የበጎ አድራጎት ድርጅት በ 2017 እና የ 2018 የስራ እንቅስቃሴው አጠቃላይ ሰነዶችን መሆኑን እየገለጽን፡ የስራ ቦታ አዲስ አበባ ላንቻ ወረዳ 04 በስተጀርባ መሆኑን አውቃችሁ በወጣው ማስታወቂያ ለመሳተፍ የሚችሉ የኦዲት አገልግሎት ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘተዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል::
1. የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ መስሪያ ቤት የተመዘገቡና ሕጋዊ የኦዲት ስራ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
2. የግብር መክፈያ ቁጥር /TIN NUMBER/ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፤
3. በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ /NGO/ ላይ 2 ሁለት እና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
4. ተጫራች ድርጅቱ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 የተዘረዘሩትን መረጃዎች እና ለስራው ያቀረበውን ዋጋ እንዲሁም ስራውን አጠናቆ የሚያስረክብበትን ጊዜ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በላይፍ ጌት የበጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ቢሮ አዲስ አበባ ላንቻ ወረዳ 04 በስተጀርባ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
5. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912408188 /0925491935 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል::
ሳይፍ ጌት የበጎ አድራጎት ድርጅት
