በጉምሩክ ኮሚሽን ኢስ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2019
የጨረታ ማስታወቂያ
በጉምሩክ ኮሚሽን ኢስ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2019 በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፥ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ሞባይሎች፡ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮ ንክስ ዕቃዎችን፤ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፥ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከህሙስ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በመሆኑም
1. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍክየከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ (C.PO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር እያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨ ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብርለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዉስት ማስገባት ይኖርበታል።
2. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
4. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS
ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ኤአ ቃሊቲ ጉምሩክቅ/ጽ/ቤት |
የዕቃ ግልፅ
|
እስከ 05/12/2018
|
06/12/2018 3:45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ |
6. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- ኢ.እ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
7. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተግለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተግለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ
ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለጉብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
10. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው:: ስተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ፡- 011-470-85-03 አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈሙ መንገድ መገንጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
በአዲስ አበባ ቃሲቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
