ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (Raw Local Coal) ግዥ
ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ሙሲ4/25/2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ያልታጠበ የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል (Raw Local Coal) (ከደቡብ ኢትዮጵያ ከልል ብቻ) መጠኑ 41,500 (አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ) ቶን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው የሚሳተፉ ደርጅት በዘርፉ የተሰማሩ አምራች ወይም አቅራቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ያላቸው አምራች ከሆናችሁ ከክልል መንግስታት የተሰጠ የማእድን ማምረት ስራ ፍቃድ ሰርተፊኬት አቅራቢ ከሆኑ የአቅራቢነት ፍቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታከስ እና የታከስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ የድንጋይ ከሰል ምርመራ ውጤት እና ይዞታ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ፤ (አስገዳጅ መስፈርት ሲሆነ አሟልቶ ያላቀረበ ከጨረታው ይሰረዛል) ስለዚህ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች (ንግድ ምዝገባ፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታከስና የታክስ ከፋይ ምዝገባ ኮፒ) በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር575.00 ከነቫቱ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ገርጂ አካባቢ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል መዳረሻ ወለል ከሚገኘው የፋብሪካው ግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ብር) በኬሚካል ኢንዳስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብርካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ CPO ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶከመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሀሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዢ መምሪያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በዕለቱ ነሀሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዢ መምሪያ ይከፈታል፣ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
