የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እና ካሜራ ዓይነቶች ግዥ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/አ/ሕ/ከ/መ/ የኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለኮንታ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ ዓይነት ግዥዎችን ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት በሎት የተለያዩ ኤሌከትሮኒከስ ሎት2 የተለያዩ ካሜራ ዓይነቶችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ስመጫረት የምትፈልጉ፡-
- የዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ
- የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት
- በዘርፉ በመንግስት ግዥ ላይ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር(ቲን ነምበር)
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ምስከር ወርቀት
- ከማንኛውም ግብርና ታክስ ዕዳ ነፃ ስለመሆኑ ከባለስልጣኑ መ/ቤት የግብርና የታከስ ኪሊራንስ ማቅረብ የሚችል
- ከዚህ በፊት ያለውን የድርጅቱ የመልካም ሥራ አፈፃፀም የ2016 ዓ/ም ወይም 2017 ዓ.ም ያለውን ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለሎት1 300,000(ሦስት መቶ ሺህ ብር) ለሎት2 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በCPO ከታወቀ ባንከ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 9 መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ በኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የጨረታ ዶከመንቶች በመግዛትና በዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት እያንዳንዱን ሎት ቴክኒካል ኦርጅናል 1 እና ቴከኒካል ኮፒ 1፤ ፋይናንሻል ኦርጅናል 1 እና ፋይናንሻል ኮፒ 2 በድምሩ 5 ፖስታ የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ በአንድ እናት የጨረታ ፖስታ በማሸግ በኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሸጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ይከፈታል፡፡
- በጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ሌሎች የመወዳደሪያ ነጥቦች (መስፈርቶች) በጨረታ ዶክመንቱ መሠረት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
- በጨረታ ማስታወቂያ እና ዶክመንቱ ላይ የተገለፁትን የመወዳደሪያ ነጥቦችን ያሟላ ተጫራች ብቻ ወደ ድህረ ግምገማ ያልፋል፡፡
- ተወዳዳሪ ተጫራቾች በጋዜጣዉ ላይ የተዘረዘሩ ነጥቦች የመገምገሚያ አካል ስለሆነ ያላሟላ ተጫራች ወደ ፋይናንሻል ማለፍ አይችልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር፡- 0917161785 / 0917388691 አድራሻችን፡- በደ/ም/ሕ/ከ/መ/ኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ከጅማ ከተማ በስተደቡብ 102 ኪሜ ርቀት ላይ ኮንታ ዞን በአመያ ከተማ ይገኛል፡፡
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ/ የኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
✨ messages.ai_summary
- Procurement of various electronics (Lot 1) and different types of cameras (Lot 2) by the Konta Zone Finance Department, South Ethiopia Regional State.
- Non-refundable bid document price: 500 ETB, available from the Konta Zone Finance Department office until the 15th day from the announcement's newspaper publication.
- Submission and opening: Bids must be submitted by 8:00 and are opened at 8:30 on the 16th day; if this falls on a non-working day, it moves to the next working day.
- Bid bond: 300,000 ETB for Lot 1 and 100,000 ETB for Lot 2, in CPO from a recognized bank.
- Required documents include a renewed trade license, trade registration certificate, supplier certificate for government procurement, TIN number, VAT registration certificate, tax clearance, and a performance certificate for 2016 or 2017 E.C.
