Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Address በምስራቅ ሸዋ ዞን ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462 -114-616
  • Website
  • Deadline25 Aug 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 500/አምስት መቶ (የማይመለስ)
  • opening dateበ16ኛው ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Categories Petroleum Products Fuel, Diesel , Oil And Lubricant

የተለያየ ዓይነት ዘይቶችና ቅባቶች ግዥ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢመአ/ሻሽ/006/2019

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2019 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ ተሽከርካሪዎችና መሣሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ ዓይነት ያላቸው ዘይቶችና ቅባቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠብቅባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርቲፍኬት እና የግብር ከፋይ ምስከር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለ2017 በጀት ዓመት ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ከሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 50.000.00(ሀምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
  4. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በአለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000002579859 ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ዕቃ ግዥ አ/ን/አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይቻላል፡፡
  7. በጨረታው መከፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን የመከፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462-114-616 መጠቀም ይችላሉ፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

✨ messages.ai_summary
- Procurement of various oils and lubricants for vehicles and equipment of the Shashemene Road Maintenance District (Ethiopian Roads Administration, Oromia). Tender reference: ERA/Shash/006/2019. - The notice is displayed for 15 consecutive days from its publication in Addis Zemen newspaper; bids close on the 16th working day at 8:00 after noon and open the same day at 8:30 in the morning (next working day if the day is a holiday or closed). - Bidders must pay a non-refundable ETB 500 for the bid document (Commercial Bank of Ethiopia account 1000002579859) and provide a bank-confirmed CPO of ETB 50,000 as a bid bond. - Required documents: renewed 2018 E.C. trade license registration, VAT certificate, tax payer registration certificate, and 2017 budget year tax clearance. Submit one original and two copies of priced financial and technical documents in separate sealed envelopes.
Save Tender

ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (Raw Local Coal) ግዥ

READ MORE
ያልታጠበ የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (Raw Local Coal) መጠን 41,500 ቶን መግዛት

READ MORE