Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት
  • Address , Phone: 0475512588
  • Website
  • Deadline03 Sep 2018, 12:00 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening dateነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋድ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
  • Categories Other , Vehicle , Agricultural Materials , Machinery And Vehicles

የእርሻ ትራክተር እና ማረሻ የማሽን የኪራይ እና የአገልግሎት ከፍያ በገባው ውል መሰረት ሊፈጽም ባለመቻሉ ምከንያት ባንኩ መልሶ የተረከባቸውንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በድርድር ጨረታ ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ይፈልጋል


የድርድር ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ስርዓት ደንበኛ የሆነው ሀርቨስት ሞደርን እርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር / ለግብር ሜካናይዜሽን ፕሮጀክት አገልግሎት ከባንኩ በኪራይ የወሰደውን የእርሻ ትራክተር እና ማረሻ የማሽን የኪራይ እና የአገልግሎት ከፍያ በገባው ውል መሰረት ሊፈጽም ባለመቻሉ ምከንያት ባንኩ መልሶ የተረከባቸውንና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በድርድር ጨረታ ለመሸጥ ወይም ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

1. የሚሸጡ / የሚከራዩ ንብረቶች ዝርዝር

ተ. ቁየተከራዩ ስምንብረቱ የሚገኝበት አድራሻየመያዣ ንብረት ዝርዝርመረጃየድርድሩ መነሻ ዋጋ ብርየድርድሩ ደረጃየድርድሩ የሚካሄድበት ቦታ ቀንና ሰዓት
1ሀርቨስት ሞደርን እርሻ ሜካናይዜሽን አገልግሎት ኃ/የተ/2/9ህበርበጋ/ሕ/ብ/ክ/መንግስት አኙዋ ዞን ጋምቤላ ከተማ የዲስትሪከት የዋስትና ንብረት ማከማቻ መጋዘን ቅጥር ግቢ ዉስጥአንድ LANDINI 2022 MODEL 133Hp Tractor እና አንድ AGRI-WAY 28 ምጣድ መከስከሻ7,265,379.06 ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ስድሳ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር ከ06 ሳንቲምጨረታ የድርድርጋምቤላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት፣ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋድ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

2. የጨረታው መመሪያ

  1. ከላይ የተመለከቱትን ንብረቶች በጥሬ ገንዘብ መግዛት ወይም መከራየት የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰቦች፣ ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የንብረቱን የድርድር መነሻ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በኢትዮጵያ ልማት ባንክስም በተዘጋጀና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በድርድሩ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ (ካሽ) ለመግዛት ተደራድሮ ያሸነፈ ተጫራች ቀሪውን ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። ካልከፈለ የድርድሩ ውጤት ተሰርዞ የተያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
  3. ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን (የንግድ ፈቃድ፣ የታደሰ መታወቂያ ወዘተ) ይዞ መቅረብ ያስፈልጋል። ድርድሩ ባልተሳካላቸው ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  4. የድርድሩ አሸናፊ ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ የሚገዛ ከሆነ ተመሳሳይከቀረጥ ነፃ የመጠቀም መብት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል። ከቀረጥ ነፃ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግሥት የሚጠበቁ ማናቸውንም ቀረጥና ሌሎች ክፍያዎች በቅድሚያ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
  5. የድርድሩ አሸናፊ ባሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% VAT (ተጨማሪ እሴት ታክስ) ጨምሮ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
  6. አሸናፊው ተጫራች ንብረቱን ለመከራየት (በሊዝ) የሚፈልግ ከሆነ ቢያንስ የማሽኑን ጠቅላላ ዋጋ 20% በቅድሚያ በመክፈል በ15 ተከታታይቀናት ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟላት የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
  7. ንብረቶችንከድርድሩ በፊትማየትወይምመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከባንኩ ጋር አስቀድመው ፕሮግራም በመያዝ መጎብኘት ይችላሉ። ተጫራቾች በሠንጠረዡ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በጋምቤላ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ በአካል ተገኝተው ድርድሩን ማካሄድ ይኖርባቸዋል።
  8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ድርድሩን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ለማንኛውም ማብራሪያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር +251475512577 / +251475512588 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት

✨ messages.ai_summary
- Negotiation tender to sell or lease repossessed assets: one LANDINI 2022 Model 133Hp tractor and one AGRI-WAY 28-disc harrow, located in the District collateral warehouse compound in Gambela city. - Issued by: Development Bank of Ethiopia, Gambela District. - Starting negotiation price is ETB 7,265,379.06; bidders must deposit 10% of this amount in cash or bank-confirmed CPO. - Negotiation is set for Nehassie 28, 2018 E.C., from 4:00 to 6:00 PM at the Gambela District office; bidders must bring a business license and renewed ID. - Cash buyers must pay the balance within 15 consecutive days plus 15% VAT; lease winners must pay at least 20% upfront and meet the bank’s machinery lease requirements.
Save Tender

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት መጠቀሚያ የሚሆን በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽ...

READ MORE
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ Core Drilling Machine with spare part...

READ MORE