የዋልማ ታፍ ነዳጅ ማደያ ግልጽ ጨረታ
አገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የዋግ ልማት ማኅበር (ዋልማ) በ2019 ዓ.ም በጀት አመት ንብረትነቱ የዋግ ልማት ማኅበር(ዋልማ) የሆነው ወይብላ ማርያም ካቴድራል ቤተ ከርስቲያን አካባቢ የሚገኘውን ዋልማ ታፍ ነዳጅ ማደያ ግልጽ ጨረታ አውጥቶ ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል (የምትችል)፡፡
- በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሠ ንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው (ያላት)፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምሥክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተወዳዳሪዎች በስማቸው የተመዘገበ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቲ መኪና ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚገዙበት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመግዛት የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጋዜጣው በወጣበት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በወጣው በ22ኛው ቀን ቢሮ ቁጥር 2 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሲል ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ልማት ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የዋግ ልማት ማኅበር (ዋልማ)
✨ messages.ai_summary
- Open national tender for the Walma Taff fuel station, located near Weibla Mariam Cathedral Church, issued by the Wag Development Association (Walma).
- Bid documents are available for a non-refundable fee of 300 ETB from Office No. 2; bids must be submitted in one or two sealed copies by the 22nd day at 4:00, with opening on the same day at 4:30.
- A bid bond of 1% of the total bid price is required, via bank-confirmed payment order (CPO), unconditional bank guarantee, or cash.
- Bidders must have a valid trade license, business registration, TIN, VAT registration, proof of current tax payment, and a fuel tanker truck registered in their own name.
