Tender Detail

Tender Details


የበቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም ለወረዳው መንግሥት መ/ቤቶች ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በሎት የተከፋፈሉትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

የበቾ ወረዳ ገንዘብ /ቤት 2019 / ለወረዳው መንግሥት /ቤቶች ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በሎት የተከፋፈሉትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1

ሎት 2

ሎት 3

ሎት 4

ሎት 5

ሎት 6

የደንብ ልብስ፣ ፍራሽና አልጋ

የጽህፈት መሳሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

የጽዳት ዕቃዎች፣ አነስተኛ ዕቃዎችና መሳሪያዎች

የመኪና ጎማ፣የተሽርካሪዎች መለዋወጫ፣ የመብራት ዕቃዎች የበርቁልፎች

ኤሌከትሮኒከስ፣ቋሚ፣ የቢሮ ዕቃዎች፣ ምንጣፎች፣ መጋረጃዎች


ሞተርብስክሌት

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢዎች የጨረታ ሰነዱን ገዝተው እንዲወዳደሩ ናስታውቃለን፡፡
1. የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ለዚህም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቲን(T) እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሁሉም ሎት አንድ ላይ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ ላይ የመንግሥትን ታክስ አካተው (ደምረውበት) ማቅረብ አለባቸው። በጨረታ ሰነድ ላይ የመንግሥት ታክስ መካተቱ (መደመሩ) ካልተገለጸ የቀረበው የጨረታ ሰነድ የመንግሥትን ታክስ እንደተካተተበት ተሰልቶ ይሰራል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋጋ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 የሰውን እያንዳንዳቸው በብር100(መቶ) በመስላት በበቾ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር1000036818909 በተከፈው ሂሳብ ገቢ በማድረግና ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣

6. የጨረታ ሠነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የሥራ ቀናትና በሥራ ሰዓት በቱሉ ቦሎ ከተማ በበቾ ወረዳ ገንዘብ /ቤት የቢሮ ቁጥር 3 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን ሠነድ ለየብቻቸው በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀን 600 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
8. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን አንስቶ 16ኛው የሥራ ቀን፣ ከቀኑ 800 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በበቾ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ቢሮ ቁጥር3 ይከፈታል። ዕለቱ የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይይከፈታል።

9. ከተገለጸው ሰዓት ውጪ የቀረበው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
10. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ማጓጓዣ (ወጪ) በቾ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
11. በጨረታ ማስታወቂያና በግዢ ጨረታ መመሪያ ላይ የተፃፉ መስፈርቶች የሚለያዩ ከሆነ በግዢ ጨረታ መመሪያ ላይ የተፃፉ መስፈርቶች ተቀባይነት ይኖራቸዋል።
12. የጥቃቅንና አነስተኛ ማይከሮ ኢንተርፕራይዝ ለውድድር የሚቀርቡት የዘመኑን ሒሣብ (2018 .)ኦዲት አስደርገው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ከዚህ በፊት ለሰሩት ስራ መልካም ስምና ተግባር ስለመኖራቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
13. ተወዳዳሪው በራሱ ስም የተከፈተውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የሲንቄ ባንከ ሂሳብ ቁጥርለብቻ ጽፈው ከግዢ ሰነድ (ከመወዳደሪያ ሀሳብ) ጋር ማስገባት ይኖርበታል።
14. /ቤቱ ከዚህ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. ማሳሰቢያ፡-ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ሳይሆን ለእያንዳንዱ ዕቃ ነጠላ ዋጋ በተሞለው ዋጋ መሠረት ነው፡፡
አድራሻ፡- በጅማ መሥመር ከአ. 80 .. ላይ ቱሉቦሎ ከተማ መናኸሪያ አከባቢ እንገኛለን።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 0113421080/0923711897/0913307562/ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።


በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የበቾ ወረዳ ገንዘብ /ቤት

✨ messages.ai_summary
Procurement of goods in six lots: uniforms/beds, office stationery, cleaning supplies, vehicle tires/spares/electrical items, electronics/furniture/carpets/curtains, and motorcycles. Bidders need valid trade license, supplier registration, and TIN/VAT certificates.
Save Tender