የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ሴክተርመ/ቤቶች ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱ ዕቃዎች እና አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ወዞፋ/ግ/01/2019
የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ሴክተርመ/ቤቶች ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱ ዕቃዎች እና አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የሚገዛው ዕቃ |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
የህትመት አገልግሎት ግዥ |
60,000 |
|
2 |
የባህል አልባሳት ግዥ |
60,000 |
|
3 |
የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ |
60,000 |
|
4 |
የዘመናዊ ሙዚቃ መሣሪያ ከነሙሉ አክሰሰሪ ግዥ |
60,000 |
|
5 |
ድሮን ግዥ |
60,000 |
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፊኬት፣ የታከስ ከፋይነት ማረጋገጫ (ቲን) ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ወይም (e-GP) ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ እና የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሠነድ እየከፈሉ ከወላይታ ዞን ፋይ/ፕ/ል/መምሪያ 2ኛ ፎቅ ከቢሮ ቁጥር 3 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የአንዱን ዕቃ ወይም አገልግሎት ግዥ ዋጋ የሚያቀርቡበትን የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው ዋጋ መሙያ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በወላይታ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በጨረታ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 19 መከተት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ 1 ኦሪጅናል እና 1 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መከተት ይኖርባቸዋል።
5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመምሪያው የጨረታ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
6. አሸናፊ ድርጅት አስፈላጊውን ውለታ በመፈጸም ዕቃውን ሙሉ በሙሉ ወላይታ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ድረስ በማቅረብ ገቢ ሲያደርግ ከፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
7. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0465512116 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
