Sale of various vehicles and motorcycles
ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2019 የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ በቢሮ፤ ዞን፣ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች እና ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤
- የኤጀንሲው አድራሻ፤ አዲስ አበባ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ / የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊትለፊት/ ፌ አናኒ ሕንጻ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከመንግሥት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር - 02 መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30- 10፡30 ሰዓት ብቻ ነው።
- የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30–10፡30 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ መነሻ ዋጋ 20% /ሃያ ከመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ CPO የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-11 557-7027
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
✨ messages.ai_summary
Open tender for the sale of various decommissioned vehicles and motorcycles owned by Oromia government offices across zones, cities, and districts. Bidders must purchase tender documents and submit sealed price offers with a 20% bid security.
