Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን
  • Address ሆሳዕና ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0910062954
  • Website
  • Deadline28 Aug 2026, 12:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 50/ሃምሳ ብር/ (የማይመለስ)
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ 08:00
  • Categories Music And Music Instrument

የተሰያዩ አይነት የማርሽ ባንድ ዕቃዎች ግዥ


በድጋሚ የወጣ የተሰያዩ አይነት የማርሽ ባንድ ዕቃዎች ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ማስታወቂያ ቁጥር (ስንድ) 01/2019

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ለ2019 በጀት ዓመት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ መልክ ለተዋቀረው የማርሽ ባንድ የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ የማርሽ ባንድ የሙዚቃ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው፣ የታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀትና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርተፍኬት ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የትብብር ደ/ቤ ማቅረብ የሚችል፣
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/Bid Bond/ ለሚያቀርቡት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% /CPO/ ወይም ሌተር አፍ ክሬዲት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቶች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው የተሞላው ዋጋ ከዘጠና ቀናት (90) በታች መሆን የለበትም፡፡
  4. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን እሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  5. የቴክኒካል ስፔስፍኬሽን እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በቅጂ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ በመከፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሠረት በግልጽ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ጨረታ የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15ኛው ቀን በኋላ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከቀኑ 06፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ 08:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  9. ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በሚዋዋልበት ጊዜ 20% የመጨመር ወይንም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ኮሚሽኑ ከአሸናፊ ተጫራቶች ጋር ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 25% የመጨመር መብት አለው፡፡

ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ሞባይል ቁጥር 0910062954 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን ሆሳዕና

✨ messages.ai_summary
Procurement of various marching band musical instruments for the newly formed band of the Central Ethiopia Regional State Police Commission. Bidders must have a valid trade license, tax clearance, VAT registration, and supplier certificate.
Save Tender